የፕሬዚዳንት ዜለንስኪ እና የጠቅላይ ሚኒስትር ስታርመር የለንደን ውይይት

Date:

የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎዲሚር ዜለንስኪ እና የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ኬይር ስታርመር በለንደን ዳውኒንግ ስትሪት ተናኝተው ተወያይተዋል። 

በዛሬው እለት ዘለንስኪ ዩናይትድ ኪንግደም ሲደርሱ በጠቅላይ ሚንስትር ስታርመር፤ ደማቅ አቀባበል እንደተደረገላቸው ቢቢሲ ዘግቧል።

ሁለቱ መሪዎች የተገናኙት ዶናልድ ትራምፕ እና ቭላድሚር ፑቲን በአላስካ ከሚያደርጉት ስብሰባ አንድ ቀን ቀደም ብሎ ነው።

ስታርመር በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል የተኩስ አቁም ለመፍጠር “እውነተኛ ዕድል” እንዳለ ከአሜሪካ – ዩክሬን ስብሰባ በፊት ጠቁመዋል።

ዜለንስኪ በበኩላቸው ዩናይትድ ስቴትስ ዩክሬንን ለመደገፍ ዝግጁ መሆኗን የገለፁ ሲሆን፤ የጀርመኑ ቻንስለር ፍሬድሪክ ሜርዝ ደግሞ የሰላም ስምምነት ካልተደረሰ በፑቲን ላይ የበለጠ ጫና እንደሚያደርጉ ቃል መግባታቸው ይታወሳል።

ዘሌንስኪ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ስታርመር ከተገናኙ በኃላ ለመገናኛ ብዙሃን ጥያቄዎች ምላሽ አልሰጡም።

ወሳኙ ስብሰባ ትራምፕ እና ፑቲን ሲገናኙ የሚደረግ ቢሆንም  ስታርመር እና ዘሌንስኪ ውይይቱ አካል አለመሆናቸው ነው የተገለፀው።

በትራምፕ እና በፑቲን መካከል በነገው እለት የሚካሄደው ውይይት በዩክሬን እና በአውሮፓ ላይ ትልቅ ተጽእኖ ሊኖረው ይችላል ተብሏል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከጥር 1 ቀን 2019 ዓ.ም. ጀምሮ ለጫት ላኪዎች የቅድመ ፈቃድ ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት መስጠት ይቆማል

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከጫት ወጪ ንግድ ፈቃድና የብቃት...

ከ4.2 ሚሊዮን በላይ ሠራተኞች ይፈለጋሉ

በኢትዮጵያ ከ4.2 ሚሊዮን በላይ ክፍት የመንግሥት የሥራ መደቦች መኖራቸውንና...

አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የሂሳብ መዝገብ ሪፖርትን እስከ ነገ በቅጣት እንደሚቀበል አስታወቀ

  የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ዓመታዊ የግብር ግዴታቸውን ያልተወጡ ግብር...

ፈንታዬ በላይነህ የቦስተን ግማሽ ማራቶንን ለሦስተኛ ተከታታይ ጊዜ አሸነፈች

በ2026 የቦስተን ግማሽ ማራቶን ውድድር በሴቶች ምድብ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት...