ዩናይትድ ኪንግደም በኢራን ባለው የጸጥታ ሁኔታ በቴህራን የሚገኙ የኤምባሲ ሰራተኞቿን ልታስወጣ መሆኑን የዩኬ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
“ሰራተኞቻችንን በጊዜያዊነት ከኢራን ለማስወጣት የጥንቃቄ እርምጃ ወስደናል” ሲል የዩናይትድ ኪንግደም የውጭ፣ የኮመንዌልዝ እና ዴቨሎፕመንት ጽህፈት ቤት በመግለጫው አስታውቋል።
ሆኖም ኤምባሲው ስራውን እንደማያቆምና “አገልግሎቱን በርቀት እንደሚሰጥ” ገልጿል።
በሳምንቱ መጀመሪያ በተመሳሳይ መልኩ በደህንንት ስጋት ምክንያት በእስራኤል የሚገኘውን ኤምባሲዋን እና የቆንስላ ሰራተኞቿን ለጊዜው እንደምታስወጣ አስታውቃለች።
BBC Amharic