የዋንዳ ዳይመንድ ሊግ ከአንድ ወር ያላነሰ የእረፍት ጊዜ በኋላ ዛሬ ቅዳሜ ወደ ውድድር ሲመለስ ኢትዮጵያዊቷን ጀግና አትሌት ጉዳፍ ፀጋይን በአሸናፊነት አንግሷል።
የአለም አይኖች ሁሉ ያረፉበት የፖላንዷ ሲሌሲያ የ1500 ሜትር ዳይመንድ ሊግ፣ አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ 3:50:73 በመግባት አሸናፈነቷን አውጃለች፡፡
ከውድድሩ በፊት ለማሸነፍ ብቻ ሳይሆን ለሪከርድም ነው የምሮጠው ያለችው ኬንያዊቷ አትሌት ባትረስ ቼቤት ከጉዳፍ አራት ሰከንድ አካባቢ ዘግይታ በመግባት በሁለተኛነት፣ ጆርጂያና ሀንተር ቤል ደግሞ በሦስተኛነት አጠናቀዋል፡፡
አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ የገባችበት 3:50:73 የሲዝኑ ምርጥ ሰዓቷም ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
- ጉዳፍ ፀጋይ 3:50.62 MR, SB
- ቤትሪስ ቼቤት 3:54.73 PB
- ጂኦርጂያ ሀንተር ቤል 3:56.00
- በጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ(ሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል)