ድንቃይ

Date:

የዓለማችን ረጅሙ ዘፈን

ብዙውን ጊዜ ብዙዎቻችን የምናዳምጠው አንድ ዘፈን ርዝማኔው ከሶስት እስከ አምስት ደቂቃ፤ ቢረዝም 10 ደቂቃ እንደሆነ ይታወቃል። እአአ “ከ2013 እስከ 2018 ባሉት አመታት በቢልቦርድ ላይ ከተቀመጡ ሙዚቃዎች መካከልም አማካይ የአንድ ዘፈን ርዝማኔ ከሶስት ደቂቃ ከ50 ሰከንድ ወደ 3 ደቂቃ ከ30 ሰከንድ መቀነሱን ኳርትዝ በ2019 ባወጣው መረጃ አስነብቧል። ረጅሙ ዘፈን ተብሎ የነበረውም የፍቅር ዘፈን ሲሆን፤ የ10 ደቂቃ ቆይታ እንደነበረው ዘገባው አመላክቷል። አልፎ አልፎም ከዚህ ዘለቅ ያለ ርዝማኔ ያላቸው ዘፈኖች ታይተዋል። የብዙ ሙያዎች ባለቤት የሆነው ህንዳዊው ጸሐፊ፣ ተመራማሪ እና አነቃቂ ንግግር አድራጊዊው ዶ/ር ጃጋዴሽ ፒላይ ከዚህ የተለየ ስራውን ይዞ ብቅ ብሎ፤ ዓለምን አስደምሟል። ያሰበውን ለማድረግ ባደረጋቸው ውጣ ውረዶች ከተጋፈጠው ረጅም ጉዞ በኋላ፤ ዶ/ር ፒላይ ረጅምም ብቻ ተብሎ የሚገለጽጸውን ሳይሆን በጣም ረጅም የሆነውን ዘፈን ይዞ ብቅ ብሏል። የዶክተር ፒላይ ዘፈን ርዝማኔ ዓለምን ጉድ አስብሎ በዓለም ድንቃድንቅ መዝገብ ላይም ሊሰፍር ችሏል። ይህ ባለ ሪከርዱ ዘፈን 138 ሰዓት ከ41 ደቂቃ ከ20 ሰከንድ ርዝመት ያለው መሆኑን ከዓለም ድንቃድንቅ መዝገብ ላይ ያገኘነው መረጀጃያሳያል። ይህ የዓለማችን ረጅሙ ዘፈን አምስት ቀናት ሳይቋረጥ መደመጥ የሚችል ነውም ተብሏል። የዘፈኑ ግጥም ከ15 ሺህ በላይ ስንኞች ያሉት ሲሆን፤ ዘፈኑን አቀናብሮ ለመጨረስ የአራት ዓመታት ከ63 ቀናት እድሜ የወሰደ መሆኑም ተገልጿል።

ከዕጽዋት አምባ

የባለጣዕሙ ቅርንፉድ ጥቅም

ቅርንፉድ ሁለገብና ጣዕምን የሚጨምር ጠቃሚ ቅመም ነው፡፡ ቅርንፉድ ፋይበር፣ ቫይታሚን እና ጠቃሚ ማዕድኖችን የያዘ ቅመም ሲሆን፥ ምግብ ላይ ጣዕም ከመጨመሩም በላይ ካንሰርን ጨምሮ በሽታን በመከላከል ለጤና ጠቃሚ መሆኑን የህክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡ አንዳንድ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ቅርንፉድ ውስጥ የሚገኙት ውህዶች ካንሰርን ለመከላከል ይረዳሉ፤ በዚህም የእጢን እድገት ይገታል፡፡

ጠቅላላ እውቀት

አስፐርቴም የተሰኘው የለስላሳ መጠጦች ማጣፈጫ ካንሰር ያመጣል? 

አስፐርቴም የተሰኘው በርካታ መጠጦች ውስጥ የሚገኝ ማጣፈጫ “ካንሰር ሊያመጣ ይችላል” ቢባልም የዓለም ጤና ድርጅት እስካሁን ምክሩን አልቀየረም። በርካታ ሰዎች አደጋ ያመጣል ከሚባለው መጠን በታች አስፐርቴም ቢወስዱም፣ ድርጅቱ በርከት አድርገው የሚወስዱ ሰዎች ጥንቃቄ እንዳይለያቸው አስጠንቅቋል። አስፐርቴም ከስኳር ነፃ በሚባሉ ምግቦች ውስጥ የሚገኝ ሲሆን በአነስተኛ ካሎሪ ከስኳር 200 እጥፍ የሆነ ጥፍጥና መስጠት ይችላል። ይህን ማጣፈጫ ከሚጠቀሙ ታዋቂ ምርቶች መካከል ዳየት ኮካ፣ ስኳር የሌለው ኮካ እና ፔፕሲ ማክስ ይገኙበታል። ነገር ግን አስፐርቴም ከማስቲካ ጀምሮ እስከ ጥርስ ሳሙና እና እርጎ ድረስ ባሉ ምርቶች ውስጥ ይገኛል። በ1980ዎቹ ለገበያ የቀረበው ይህ ኬሚካል በስፋት ጥቅም ላይ ቢውልም አሁን አከራካሪ ምርት ነው። በዓለም ጤና ድርጅት የኒውትሪሽንና ምግብ ደኅንነት ክፍል ኃላፊ የሆኑት ዶክተር ፍራንቼስኮ ብራንካ ጤናማው ምርጫ ስኳር ወይስ ማጣፈጫ ተብለው ተጠይቀው፣“ምርጫ ቀርቦ ኮላ በማጣፈጫ ይሁን አሊያም በስኳር ቢባልማ እኔ ሦስተኛ ምርጫ ኖሮ ውሃ ብጠጣ እመርጣለሁ። አሊያም ማጣፈጫ የገባባቸው ምርቶች በገደብ መጠቀም ይገባል።” ብለዋል። ዶክተሩ እንደሚሉት ጥናቶቹ ሲመረመሩ አስፐርቴም ለጤና ጠቃሚ ላይሆን እንደሚችል ይጠቁማሉ። ነገር ግን አንዳንዴ የምንጠጣው ከስኳር ነጻ የሆነውና የካሎሪ መጠኑ ዝቅተኛ የሆነው ዳየት ኮካ ሳይሆን ሊያሳስበን የሚገባው በጣም በተደጋጋሚ የምንጠቀም ከሆነ ነው ይላሉ።

የዓለም ጤና ድርጅት አካል የሆነው ዓለም አቀፉ የካንሰር ጥናት ኤጀንሲ አስፐርቴም “ካንሰር ሊያመጣ የሚችል ነው” የሚል መደመደሚያ ላይ ደርሷል። ይህ ድምዳሜ ላይ የደረሰው ማጣፈጫው የጉበት ካንሰር ሊያመጣ ይችላል የሚሉ ሦስት ጥናቶችን መሠረት አድርጎ ነው። ነገር ግን ይህን ለማረጋገጥ ጠንከር ያለ ሳይንሳዊ ማስረጃ ማቅረብ ያስፈልጋል። የካንሰር ጥናት ኤጀንሲው ሠራተኛ የሆኑት ዶክተር ሜሪ ሹባወር-ቤሪጋን “አሁን ያለው ማስረጃ ጥራት ያለውና ጠንካራ ነው ማለት ከባድ ነው” ይላሉ። የዓለም ጤና ድርጅት ይህ ማጣፈጫ “ለካንሰር ሊያጋልጥ ይችላል” ቢልም በፈረንጆቹ 1981 የወጣን ምክር እስካሁን አልቀየረም። ይህ ማለት በቀን በአንድ ኪሎ ግራም የሰውነት ክብደት 40 ሚሊግራም ነው መውሰድ የሚመከረው። ይህን አድርጉ ማለት አይደለም። ከዚህ በላይ እንዳታደርጉ እንጂ የሚል ነው የጤና ድርጅቱ ምክር። ነገር ግን የምንለካው በሰውነት ክብደታችን ከሆነ ሕፃናት ሊጎዱ ይችላሉ። ዶክተር ብራንካ ጣፋጭ መጠጥ ሕፃናት ባሉበት ለእራት ማቅረብ ቢቀርብን የሚል ምክር ይለግሳሉ። አክለው ማጣፈጫዎች ክብደት ይቀንሳሉ የሚባለው በፍፁም ሐሰት ነው ይላሉ። በጠቅላላው ምክራቸው ከስኳርም ሆነ ከማጣፈጫ ራሳችን በተቻለ መጠን ገለል እናድርግ ነው።

BBC

የወንጀል ጥግ

እየሱስ ነኝ በሚል 300 ሺህ ዩሮ የተቀበለው አጭበርባሪ ተያዘ፡-

ግለሰቡ አዛውንቷን በገነት ውስጥ ለምታሳልፊው ህይወት ወጪ ይሆንሻል በሚል ገንዘቡን እሱ ጋር እንድታስቀምጥ አድርጓል ተብሏል፤ እየሱስ ነኝ በሚል 300 ሺህ ዩሮ የተቀበለው አጭበርባሪ ተያዘ። በሀገረ ስፔን እኔ እየሱስ ነኝ በሚል አንድ አዛውንትን በማጭበርበር ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ እንደተቀበለ ተገልጿል። ግለሰቡ አዛውንቷን በገነት ህይወትሽ ለሚያስፈልጉሽ አንዳንድ ነገሮች በከፍተኛ ወለድ ያላትን ገንዘብ እሱ ባዘጋጀው አነስተኛ እቃ ውስጥ እንድትቆጥብ እድርጋል ተብሏል። እስፔራንዛ የተሳኙት እኝህ አዛውንትም ከእየሱስ እንደተደወለላት፣ ገነት እንደምትገባ እና ገንዘቧን እንድትቆጥብ እንደተነገራት ለቤተሰቦቿ መናገራም ተገልጿል። አዛውንቷ ሴትዮም እራሱን እየሱስ ነኝ በሚለው ግለሰብ በመታለል ላለፉት ስድስት ዓመታት ያላትን ገንዘብ ሁሉ እያወጣች ሰጥታለች ተብሏል። ግለሰቧ ከፈረንጆቹ 2013 ጀምሮ እየሱስ ነኝ ብሎ ለነገራቸው ግለሰብ ገንዘባን ስትሰጥ ቆይታለች ሲል ኦዲቲ ሴንትራል ዘግባል። አዛውንቷ ከእሷ በተጨማሪም ለሴት ልጇም ቅዱስ እንደሆነች ስትነግራት ቆይታለች የተባለ ሲሆን ልጅቷ ግን እንደ እናቷ አለመታለሏ ተገልጿል። በገነት ውስጥ የተንደላቀቀ ህይወት ለማሳለፍ ቁጠባ ጀምሬያለሁ ያለችው ይህች ግለሰብም በሁለት ባንኮች ውስጥ የነበራትን ገንዘብ ሳይቀር እያወጣች እየሱስ ነኝ የሚለው ሰው ባዘጋጀላት ማጠራቀሚያ እቃ ውስጥ ስታስቀምጥ እንደቆየችም ገልጻለች። እራሱን እየሱስ ነኝ በሚል ማጭበርበሩ የተደረሰበት ግለሰብም ወንጀል እንዳልፈጸመ ቢከራከርም የሀገሪቱ መርማሪ ባደረጋቸው የስልክ እና ሌላሎች ምርመራዎች ጥፋተኛ ኮኖ ተገኝቷል ተብሏል። የስፔን ፍርድ ቤት ግለሰቡ የአዛውንቷን በእድሜ መግፋት እና የማሰላሰል አቅምን በመጠቀም በማጭበትበር ወንጀል የስምንት ዓመት እስር ተላልፎበታል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኢትዮጵያ፣ የኤርትራና የህወሓት የቃላት ጦርነት ንሯል።ይዋጉ ይሆን?

ሶስቱም ኃይላት የጦር ኃይላቸዉን እያጠናከሩ፣ አዳዲስ ተዋጊ እየመለመሉ መሆናቸዉ...

የሐማስ ታጣቂዎች ከእስራኤል ጋር በመተባበር የተከሰሱ ሰባት ሰዎችን ገደሉ

ሰኞ እለት በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ እየተዘዋወረ ያለ ቪዲዮ እንደሚያሳየው...