ጀግና በጦር ሜዳ ብቻ አይደለም የሚፈጠረው

Date:


የኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽነር ለሊሴ የካንሰር ሕመምን በጀግንነት እየተጋፈጡ ነው!

የኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽን መሪና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተፅዕኖ ፈጣሪ ከሆኑ ሴቶች መካከል አንዷ የሆኑት ኮሚሽነር ለሊሴ ጂማ የካንሰር ምርመራ እንደተደረገላቸውና ኬሞቴራፒ ሕክምና እየተከታተሉ መሆኑ ተሰማ።

ኮሚሽነር ለሊሴ ይህንን አስቸጋሪ እውነት በራሳቸው የማህበራዊ ትስስር ገጽ ላይ “እየተዋጋሁ ነው!” (“Fighting”) በሚል መልእክት ይፋ አድርገዋል። ይህ የድፍረት ቃል ተስፋንና ጽናትን ለአድናቂዎቻቸው አስተላልፏል።

የኬሞቴራፒ ሕክምና ደግሞ ጸጉርን ጨምሮ በሰውነት ላይ ባሉ ፀጉሮች ላይ መርገፍ ሊያስከትል ይችላል።

ሆኖም ግን፣ ሕዝቡ እያስተላለፈ ያለው መልእክት፦

“የእርሶ እውነተኛ ብርሃን የሚመነጨው ከአዕምሮዎ፣ ከልብዎ እና ለክልሉ ካበረከቱት አስተዋጽዖ ነው። ውጫዊ ነገር ሁሉ በዚህ የጀግንነት ትግል ፊት ዋጋ የለውም።” የሚል ነው።

ኮሚሽነር ለሊሴ ለኦሮሚያ እድገት ቁልፍ ሰው ከመሆናቸውም በላይ ለብዙዎች የአርአያነት ምንጭ ናቸው። በፍጥነት እንዲድኑ እና ሙሉ ጤንነታቸው እንዲመለስ እንመኛለን።

ፈጣሪ በምህረቱ ይፈውስዎ ኮሚሽነር

[ የክብርት ኮምሽነሯን የጀግንነት ውሳኔ እንደ ቀላል አናየውም ። የስኳር ህመም እንዳለብኝ በግልጽ ማንም ሳይጠይቀኝ ስናገር እንኳ ብዙዎች ይገረማሉ ።

ምክንያትን ስኳርና ደም ግፊትን አይነት ህመሞችን እንኳ ለቅርብ ሰዎቻቸው ጭምር ደብቀው ለሞት የተዳረጉ በቅርብ የማውቃቸው ሰዎች አሉ ፤ እኔ ብቻም ሳልሆን ብዙው የጥበብ አድናቂም የሚያውቃቸው ። ካንሰር ገና ህብረተሰባችን ያለመደው ፣ ግን በብዛት የሚገጥም ህመም ነው ። ክብርት ኮምሽነሯ ጉዳዩን አደባባይ ላይ መግለጻቸው የሚገፈው የፍርሀት መጋረጃ አለ ።

ኤችአይቪ/ኤድስን በፈቃዳቸው መደማቸው እንደሚገኝ የገለጹ የመጀመሪያዎቹ ወገኖቻችን በሽታውን ለመከላከል የነበራቸው አስተዋጽዖ ከሳይንሳዊ ግኝቶችና ከየትኛውም የመከላከያ ዘዴ በላይ ነበር ። የክብርት ኮምሽነር ሊሴ ጅማ ይህ ውሳኔ ከጀግንነት ምድብ ውስጥ የሚገባ ነው ። እናመሰግናለን ክብርት ኮምሽነር ። ፈጣሪ ምህረቱን ይላክልዎ ። 👌❤🙏 ]
ከቴዎድሮስ ተ/አረጋይ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኢትዮጵያ መልክ የሚያሳዩ የአደባባይ ሐውልቶች

በኢትዮጵያ በተለይም በመዲናዋ ውስጥ የታሪክ ምዕራፎችን በአደባባይ ቆመው የሚያስመለክቱ፣...

እድሜያቸው 12 እና 13 የሆኑ ህፃናት በስኳር በሽታ ኩላሊታቸው እንዳይሰራ እየሆነ ነው

ተላላፊ ላልሆኑ በሽታዎች የሚያጋልጡ የታሸጉ ምግቦችን ለመቆጣጠር የሚያስችል አዋጅ...

ከፍተኛ ተወዳዳሪነት በታየበት ጨረታ አሸናፊዎች ውል እንዲፈፅሙ ተጠየቀ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ በከተማው...

ሰማያዊ የመኪና መንገዶች

የዓለም የሙቀት መጠን መጨመር በተለይም በመካከለኛው ምስራቅ ያሉ ከተሞች ...