‘ጋዛ እየነደደች ነው’ – የእስራአል የመከላከያ ሚኒስትር

Date:

ከአንድ ሳምንት በኋላ ሁለት ዓመት የሚሞላው እስራኤል በጋዛ ላይ እያካሄደችው ያለው መጠነ ሰፊ ወታደራዊ ዘመቻ አሁን ተባብሶ ቀጥሏል።

እስራኤል ጋዛን ለመቆጣጠር ባወጣችው ዕቅድ መሠረት፣ ከባድ የአየር ድብደባና የእግረኛ ሠራዊት ጥቃት በጋዛ ላይ መክፈቷን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

በዚህም ጋዛ ውስጥ ያሉ ሕንጻዎች በእስራኤል የጦር አውሮፕላኖች እየወደሙ ሲሆን፣ ይህንንም የእስራአል የመከላከያ ሚኒስትር ኢዝራኤል ካትዝ፤ “ጋዛ እየነደደች ነው” ሲሉ ገልጸውታል።

መስከረም 26 ቀን 2016 ዓ.ም. ሐማስ ባልተጠበቀ ሁኔታ በእስራኤል ላይ የፈጸመውን ጥቃት ተከትሎ፣ 1200 ሰዎችን ከገደለና 251 ሰዎችን ካገተ በኋላ እስራኤል በጋዛ ላይ ከባድ ጥቃት ስትፈጽም ቆይታለች።

በሐማስ የሚመራው የጋዛ ጤና ሚኒስቴር እንዳለው፤ ከ60 ሺህ በላይ የጋዛ ነዋሪዎች ተገድለዋል። አሁን የተከፈተው ጥቃት ደግሞ የሚሞቱትን ሰዎች ቁጥር እንደሚጨምረው ተሰግቷል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ4.2 ሚሊዮን በላይ ሠራተኞች ይፈለጋሉ

በኢትዮጵያ ከ4.2 ሚሊዮን በላይ ክፍት የመንግሥት የሥራ መደቦች መኖራቸውንና...

አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የሂሳብ መዝገብ ሪፖርትን እስከ ነገ በቅጣት እንደሚቀበል አስታወቀ

  የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ዓመታዊ የግብር ግዴታቸውን ያልተወጡ ግብር...

ፈንታዬ በላይነህ የቦስተን ግማሽ ማራቶንን ለሦስተኛ ተከታታይ ጊዜ አሸነፈች

በ2026 የቦስተን ግማሽ ማራቶን ውድድር በሴቶች ምድብ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት...