ግለሰቦቸና ተቋማት ራሳቸውን ከሳይበር ጥቃት ይከላከሉ ‎

Date:


‎ግለሰቦቸ እና ተቋማት ራሳቸውን ከሳይበር ጥቃት እንዲከላከሉ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢንሳ) አሳስቧል፡፡

‎በአስተዳደሩ የተቀናጀ የሳይበር መከላከል አገልግሎት ዲቪዥን ሃላፊ አቶ አቤል ተመስገን እንዳሉት÷ የሰው ሰራሽ አስተውሎት እየተስፋፋ መሆኑን ተከትሎ የሳይበር ጥቃቶች ውስብስብ እየሆኑ መጥተዋል፡፡

‎በኢትዮጵያ የሳይበር ጥቃት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ እንደሚገኝ ጠቅሰው÷ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ብቻ 7 ሺህ 514 የጥቃት ሙከራዎች መደረጋቸውን ተናግረዋል፡፡

‎እነዚህ ጥቃቶች አብዛኞዎቹ በግለሰብ እና ተቋማት ላይ የተሞከሩ መሆናቸውን ያስረዱት ሃላፊው ÷ ግለሰቦቸ እና ተቋማት ራሳቸውን ከሳይበር ጥቃት መከላከል የሚያስችል ግንዛቤ እና አቅም ሊኖራቸው እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

‎በተለይም ግለሰቦች በቴሌግራም የሚላኩ ያልታወቁ ሊንኮችን ባለመክፈት፣ የይለፍ ቃላቸውን በማዘመን እንዲሁም በሰው ሰራሽ አስተውሎት የሚተላለፉ ሀሰተኛ ምስሎችንና መረጃዎችን በመለየት ራሳቸውን ከጥቃት መከላከል እንደሚችሉ አብራርተዋል፡፡

‎FMC

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ለሊት እንቅልፍ የለኝም

"አሁን ኢትዮጵያ ያለችበት ሁኔታ ያሳስበኛል፤ እኔ አሁን 86 ዓመት...

አዎ ነበሩ ….

🔘የሁሉም አባት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሓጅ ዑመር🔘ነፍስዎ በሰላም ትረፍ "...

ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስን ሳር ቅጠሉ የሚወዳቸው

ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስን ሳር ቅጠሉ የሚወዳቸው የሀይማኖት...