እስራኤል እና ግብፅ በታሪካችን ትልቅ የተባለው የተፈጥሮ ጋዝ ሽያጭ ስምምነት መፈራረማቸው ተሰምቷል ።
የእስራኤል ሌዋታን የተፈጥሮ ጋዝ ማዉጫ በሀገሪቱ ታሪክ ውስጥ ትልቁን የኤክስፖርት ስምምነት የተፈራረመ ሲሆን፥ እስከ 2040 ድረስ 35 ቢሊየን ዶላር የሚደርስ ዋጋ የሚያወጣ ጋዝ ለግብፅ ለማቅረብ ተስማምቷል። ይህ አዲስ ስምምነትም በግብፅ ያለውን የሃይል ቀውስ ያቃልላል ተብሏል ።
ግብፅ እ.ኤ.አ. በ 2022 ጀምሮ በከርሰ ምድሯ የሚገኘዉ የተፈጥሮ ጋዝ ማሽቆልቆሉን ተከትሎ ጉድለቶቿን ለማካካስ ወደ እስራኤል ፊቷን ማዞሯ ይታወቃል ።
ይህን ተከትሎም አዳዲስ ስምምነቶችን እያደረገች ሲሆን ሐሙስ በተገለጸው ውል መሠረት፣ በ ሜዲትራኒያን ባህር ዳርቻ፣ 600 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ክምችት ያለው ሌዋታን ጋዝ ማዉጫ ተቋም እስከ 2040 ድረስ 130 ቢ.ሲ.ሜ ጋዝ ለግብፅ ለማቅረብ ታቅዷል ።
በሀሙሱ ውል መሰረት እ.ኤ.አ. በ2020 ጀምሮ የሀገሪቱን ፍላጎት እያሟላ የሚገኘዉ የሌዋታን ማጠራቀሚያ ለግብፅን እያቀረበበት በሚገኘው በሁለቱ ሀገራት በቧንቧ መስመር በኩል 2026 መጀመሪያ ጀምሮ እስራኤል የመጀመሪያውን ደረጃ 20 ቢ.ሲ.ሜ ጋዝ ለግብፅ የሚያደርስ ሲሆን በሁለተኛው ምዕራፍ አዳዲስ መስመሮችን በመዘርጋት በእጥፍ ያቀርባል ።
በአሁኑ ስምምነት መሰረትም በሚቀጥለው አመት መጀመሪያ ላይ ከእስራኤል ወደ ግብፅ የሚደረገውን የጋዝ አቅርቦት ፍሰቱን ከ4.5 ቢ.ሴ.ሜ ወደ 6.5 ቢ.ሴ. ያድጋል ። ይህ ደግሞ የጋዝ ምርቷን ለማሳደግ አቅርቦት ለማግኘት ስትታገል ለቆየችው ግብፅ ከነበረዉ በእጥፍ 40% በማደግ የአቅርቦት እጥረት እንዳይገጥማት እፎይታ ያስገኛል ተብሏል ።
የኒውሜድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዮሲ አቡ ሐሙስ ዕለት ለሮይተርስ በሰጡት ቃለ ምልልስ “ከሌሎች LNG አማራጮች በተሻለ ይህ ከእስራኤል ጋር ያደረግነው ስምምነት እጅግ በጣም ጥሩ ነው ፣ እናም በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ዶላሮችን ለግብፅ ኢኮኖሚ ያድናል” ብለዋል ።
የእስራኤል ጋዝ አቅርቦት ከ15-20% የሚሆነውን የግብፅ ፍጆታ ይይዛል የሚለዉ ኢኒሼቲቭ የተገኘው ከጋራ ድርጅቶች መረጃ የሚያሳይ ሲሆን ወደ 2.4 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋው የሌቪያታን ማስፋፊያ እየገነባች የምትገኘው እስራኤል ለዮርዳኖስና ከግብፅ በተጨማሪ ለጎረቤቶቿ ምርትና አቅርቦቶችን መፍቀድ አለበት ሲል ተንታኙ ኒውሜድ ለሮይተርስ ተናግሯል።
(የኔታ ቲዮብ )
ግብፅና እስራኤል በታሪካቸው ትልቁን ስምምነት ተፈራረሙ !!
Date:
