ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሐጅ ኡመር ኢድሪስ ህልፈት የተሰማቸውን ኀዘን ገለፁ

Date:

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቀድሞ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝደንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ኡመር ኢድሪስ ህልፈት የተሰማቸውን ኀዘን ገልጸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባስተላለፉት የሀዘን መግለጫ፤ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ፕሬዚዳንት የነበሩት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ በማረፋቸው ኀዘን ተሰምቶኛል ብለዋል።

ሐጂ ዑመር በአመራር ዘመናቸው የተለያዩ ወገኖች ወደ አንድነት እንዲመጡ እና የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በሕግ ዕውቅና እንዲኖረው ያደረጉትን አስተዋጽዖ ሁሌም እናስታውሰዋለን ሲሉ ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለሐጅ ኡመር ኢድሪስ ቤተሰቦች እና ለመላ ኢትዮጵያ ሙስሊሞች መጽናናትን ተመኝተዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ለሊት እንቅልፍ የለኝም

"አሁን ኢትዮጵያ ያለችበት ሁኔታ ያሳስበኛል፤ እኔ አሁን 86 ዓመት...

አዎ ነበሩ ….

🔘የሁሉም አባት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሓጅ ዑመር🔘ነፍስዎ በሰላም ትረፍ "...

ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስን ሳር ቅጠሉ የሚወዳቸው

ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስን ሳር ቅጠሉ የሚወዳቸው የሀይማኖት...