ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ እና ፕሬዚዳንት አልሲሲ ፊት ለፊት ሊገናኙ?

Date:

አብይ አህመድ እና አበዱልፈታህ አልሲሲ ፊትለፊት እንዲገናኙ እንደምትፈልግ አሜሪካ አስታወቀች፡፡ የግደቡ ጉዳይ የትራምፕ ዋና አጀንዳ እንደሆነም አማካሪያቸው ይፋ አድርገዋል፡፡

አማካሪው በትራምፕ ውትወታ ካይሮ እና አዲስአበባ ሊፈርሙ ተቃርበው ስለነበረው ስምምነትም ለመጀመሪያ ጊዜ ተናግረዋል፡፡ ዋሽንግተን ሲሲ እና አብይ እንዲገናኙ እፈልጋለሁ ያለችው ግብጽ ኢትዮጵያ ላይ ወታደራዊ ማስፈራሪያ ባሰማች ማግስት ነው፡፡

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት የአፍሪካ፣ የአረብ እና የመካከለኛው ምሥራቅ ከፍተኛ አማካሪው ለሳዑዲው አል አረቢያ እንደተናገሩት፤ ትራምፕ ከመጀመሪያው የሥልጣን ዘመናቸው አንስቶ በግድቡ ዙሪያ የበኩላቸውን ሲያከናውኑ ነበር።

የፕሬዝዳንቱ አማካሪ፤ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ጉዳይ የትራምፕ ትኩረት እንዳለው በመጥቀስ ወሳኝ አጀንዳ መሆኑን ተናግረዋል።

“በመጀመሪው የፕሬዝዳንትንት ዘመናቸው ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከስምምነት እንዲደረስ ጥረት ማድረጋቸው ይታወቃል” በማለት በአገራቱ መካከል ቴክኒካዊ ስምምነት ሊፈረም ተቃርቦ በተወሰኑ ችግሮች ምክንያት መደናቀፉን አስታውሰዋል።

በወቅቱ በአሜሪካ እና በዓለም ባንክ አማካይነት በተደረገው ድርድር የተዘጋጀው ሰነድ ይፈረማል ተብሎ በሚጠበቅበት ወቅት ኢትዮጵያ የቀረበው ሰነድ ጥቅሟን አሳልፎ የሚሰጥ መሆኑን በመጥቀስ ከስምምነቱ ወጥታለች።

በዚህ የተቆጡት ፕሬዝዳንት ትራምፕ አገራቸው ለኢትዮጵያ ትሰጥ ከነበረው ድጋፍ ወደ አምስት መቶ ሚሊዮን ዶላር የሚደርሰው እንዲቋረጥ አድርገው ነበር።

ቡሎስ ሰኞ ዕለት ለአል አረቢያ፤ ሁለቱ አገራት “ወደ ግጭት ማምራት የሌለበት ታሪካዊ ትስስር አላቸው” በማለት አሁንም አሜሪካ በአዲስ አበባ እና በካይሮ መካከል ሰላማዊ ትብብር እንዲኖር እንደምታበረታታ ጠቅሰዋል፡፡

ቡሎስ “ጉዳዩ በግልጽ ቴክኒካዊ ከመሆኑ አንጻር በተለይ በቴክኒካዊው ነጥብ ሁሉንም የሚያስማማ መፍትሄ ለማግኘት እየሠራን ነው” ሲሉ ለአል አረቢያ ተናግረዋል።

በሕዳሴ ግድብ ምክንያት በኢትዮጵያ፣ በሱዳን እና በግብፅ መካከል የተከሰተውን ውዝግብ “የሞት እና የሕይወት” ጉዳይ በማለት የገለጹት ከገፍተኛ አማካሪው፤ የግድቡ ግንባታ ተጠናቅቆ ከተመረቀ በኋላ “አሁን ተጨባጭ እውነታ ሆኗል” በማለት “መፍትሄውም ከዚሁ እውነታ በመነሳት መገኘት አለበት” ብለዋል።

በግብፁ ፕሬዝዳንት እና በኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር መካከል ንግግር እንዲካሄድ ትራምፕ ጥረት ያደርጉ እንደሆነ በአል አረቢያ የተጠየቁት ቡሎስ፤ “እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ሁለቱን [መሪዎች] አብረው እናያቸው ይሆናል።

ለዚያም እየሠራን ነው” በማለት መልሰዋል። ጨምረውም እንዲህ ዓይነቱ ግንኙነት “በአፍሪካ ማዕቀፍ፣ ምናልባትም ከአፍሪካ ኅብረት ጋር በሚዛመዱ ዝግጅቶች ላይ ሊካሄድ ይችላል” በማለት አሜሪካ ቀውሱን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የሚደረጉ ማንኛውንም ጥረቶች እንድምትደግፍ ገልጸዋል። የሕዳሴው ግድብ ውዝግብ ለኢትዮጵያ፣ ለግብፅ እና ለሱዳን “የሞት ሽረት” ጉዳይ በመሆኑ ሰላማዊ መፍትሄ ያስፈልገዋል ብለዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ብሔራዊ ፈተና የወሰዳችሁ

በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ወስዳችሁ ለትምህርት...

የክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር የሰራዊት አባላት ተጠቃሚ የሚያረጋግጥ ደንብ ማጸደቁ አስታውቋል

እሁድ ጥቅምት 3/2018 ዓ.ም የጀመረው የትግራይ ኃይል ሰልፍና ተቃውሞ...

የኬንያ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ ስርዓተ ቀብር ተፈፀመ

በ80 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት የኬንያ የቀድሞ...