የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ስሕተቱን አመነ
በትናትናው ዕለት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ/ዶ/ር/ በፌስቡክ ገፃቸው እና በቲዊተር አካውንታቸው ላይ “የአፕል ግብርና ምርታማነታችን እድገት እያሳየ ነው” ከሚል ፅሁፍ ጋር ስድስት የአፕል ምስሎችን አያይዘው ለጥፈው የነበረ ቢሆንም የለጠፉት የአፕል ምስሎች ከሌላ ሀገር የተወሰዱ መሆናቸውን ተከትሎ በዛሬው ዕለት ልጥፉ ከገፃቸው ላይ መነሳቱን የጠቅላይ ሚኒስቴር ፅህፈት ቤት አሳውቋል።
ስህተቱ የተፈጠረው የታችኛው መዋቅር ወደ ጠቅላይ ሚኒስቴር ፅህፈት ቤት የተሳሳተ መረጃ በመስጠታቸው ነው ብሏል።
ምስሎቹ ከሌላ ሀገር መወሰዳቸውን ጥቆማ ላደረሱና እና እርምት እንድንወስድ ለጠየቁ አካላት የጠቅላይ ሚኒስቴር ፅህፈት ቤት ምስጋና አቅርቧል።