ኢትዮጵያ ከአፍሪካ የበሽታዎች መከላከያና መቆጣጠሪያ ማዕከል (Africa CDC) ጋር በመተባበር 5ኛውን ዓለም አቀፍ የአፍሪካ የህብረተሰብ ጤና ጉባኤ (CPHIA 2026) ከዛሬ ኅዳር 14 እስከ 18 ቀን 2019 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ታስተናግዳለች።
ጉባኤው የአፍሪካን የጤና ሥርዓት ማጠናከር፣ የህብረተሰብ ጤና ተግዳሮቶችን መቋቋምና በጤና ዘርፍ የሀገራትን ትብብር ማሳደግ ያለመ ሲሆን፣ ከአፍሪካና ከዓለም የተለያዩ የጤና ባለሙያዎች፣ የፖሊሲ አውጪዎችና ተቋማት ተወካዮች ይሳተፋሉ።
