የሁቲዎች አዲስ ትዕዛዝ

Date:

የየመን ሁቲዎች ከእስራኤል ወደቦች ጋር ስምምነት ያለው የትኛውም መርከብ እንደሚመታ አስጠነቀቁ።

”የየትኛውም ኩባንያ መርከብ በየትኛውም አገር ሰንደቅ ዓላማ ስም ይንቀሳቀስ ዒላማ ይሆናል” በሚል ዝተዋል።

ሁቲዎች ወደ 4ኛው ምዕራፍ  የእስራኤል የባህር እንቅስቃሴን  መዝጋት እርምጃ እንደሚገቡ በወታደራዊ ቃል አቀባያቸው ያህያ ሳሬ በኩል ይፋ አድርገዋል።

የሁቲ ሀይል የጦር መሳሪያ መድረስ በሚችልበት ቦታ ሁሉ መርከቦቹ ይመታሉ ነው ጥቅል ሀሳቡ።

እሁድ አመሻሹን መግለጫ የሰጠው ሁቲ አሁንም ለፍልስጤማውያን ያለውን አጋርነት አጠናክሮ እንደሚገፋበት ግልጽ አድርጓል።

ከቴል አቪቭ ጋር ስምምነት ያለው መርከብ ሁሉ ዒላማ እንደሚደረግ አንስራላሆች አረጋግጠዋል።

በተጨማሪም በቀይ ባህር እና ህንድ ውቅያኖስ በኩል በተለይም በበብ-ኤል መንደብ ሰርጥ መርከቦች እንዳይንቀሳቀሱ አድርገው መሰንበታቸውም አይዘነጋም።

በዓመት ከ1  ትሪሊዬን ዶላር በላይ ምርት ይተላለፍበታል በሚባለው ቀጠና ላይ ከባድ ጫና ሲያሳድሩም ቆይተዋል።

የመርከቦችን ጉዞም በኬፕ ኦፍ ጉድ ሆፕ ደቡባዊ አፍሪካ ጫፍ እንዲሆን በማስገደድ የቀይ ባህርን የንግድ ታሪክ 155 ዓመታት ወደ ኋላ መልሰውታል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ4.2 ሚሊዮን በላይ ሠራተኞች ይፈለጋሉ

በኢትዮጵያ ከ4.2 ሚሊዮን በላይ ክፍት የመንግሥት የሥራ መደቦች መኖራቸውንና...

አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የሂሳብ መዝገብ ሪፖርትን እስከ ነገ በቅጣት እንደሚቀበል አስታወቀ

  የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ዓመታዊ የግብር ግዴታቸውን ያልተወጡ ግብር...

ፈንታዬ በላይነህ የቦስተን ግማሽ ማራቶንን ለሦስተኛ ተከታታይ ጊዜ አሸነፈች

በ2026 የቦስተን ግማሽ ማራቶን ውድድር በሴቶች ምድብ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት...