ግብፅ እና አሜሪካ በውሃ ደህንነት እና ቁልፍ በሆኑ ቀጠናዊ ጉዳዮች ዙርያ መከሩ

Date:

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩብዮ ከግብጹ አቻቸው ባድር አብደላቲ ጋር በግብጽ የውሃ ደህንነት ዙርያ እንዲሁም በመካከላኛው ምስራቅ ሰላማን ለማስፈን በሚደረጉ ጥረቶች እና ቁልፍ በሆኑ ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውን የአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት አስታወቀ።

ሚኒስትሮቹ ረቡዕ ሐምሌ 23 ቀን 2017 ዓ.ም  ባደረጉት ስብሰባ ላይ ሩቢዮ፤ “ግብፅ በሐማስ ተይዘው የነበሩ ታጋቾችን ለማስለቀቅ ላሳየችው ጽኑ ድጋፍ” ለአብደላቲ ምስጋና አቅርበዋል ሲል የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በመግለጫው አስነብቧል።

በተጨማሪም በሱዳን ወደ ሲቪል አስተዳደር ስለሚደረገው ሽግግር አስፈላጊነትም ተወያይተዋል ሲል መስሪያ ቤቱ አክሎ ገልጿል።

የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባድር አብደላቲ ስብሰባውን አስመልክቶ በኤክስ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሑፍ፣ ከአሜሪካ አቻቸው ጋር ስትራቴጂካዊ አጋርነትን በማጠናከር፣ ቁልፍ በሆኑ ቀጠናዊ ጉዳዮች እና በግብፅ የውሃ ደህንነት ዙርያ መምከራቸውን ገልጸዋል።

ሁለቱ ሚኒስትሮች ውይይቱን ያካሄዱት በጋዛ ስላለው ረሃብ አስመልክቶ ከሰብአዊ እርዳታ ድርጅቶች በኩል የሚደረጉ ጥሪዎች እየተበራከቱ በመጡበት በአሁኑ ወቅት ነው።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ4.2 ሚሊዮን በላይ ሠራተኞች ይፈለጋሉ

በኢትዮጵያ ከ4.2 ሚሊዮን በላይ ክፍት የመንግሥት የሥራ መደቦች መኖራቸውንና...

አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የሂሳብ መዝገብ ሪፖርትን እስከ ነገ በቅጣት እንደሚቀበል አስታወቀ

  የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ዓመታዊ የግብር ግዴታቸውን ያልተወጡ ግብር...

ፈንታዬ በላይነህ የቦስተን ግማሽ ማራቶንን ለሦስተኛ ተከታታይ ጊዜ አሸነፈች

በ2026 የቦስተን ግማሽ ማራቶን ውድድር በሴቶች ምድብ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት...