በ2024 የዓለም አቀፍ የልግስና ሪፖርት መሠረት፣ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ለጋስነት 22ኛ ደረጃ ላይ ስትቀመጥ፣ የአፍሪካ አህጉር ደግሞ በዓለም ቀዳሚዋ ለጋስ አህጉር ሆና ተመዝግባለች።
የቻሪቲስ ኤድ ፋውንዴሽን (CAF) ባወጣው ሪፖርት መሠረት፣ ኢትዮጵያውያን በ2024 ዓ.ም. በአማካይ 1.51 በመቶ ገቢያቸውን ለበጎ አድራጎት፣ ለቀጥታ እርዳታ እና ለሃይማኖታዊ ልግስና አውለዋል።
ሪፖርቱ አፍሪካውያን ከሌሎች አህጉራት ጋር ሲነጻጸር በከፍተኛ ሁኔታ ከገቢያቸው የበለጠውን ክፍል ለልግስና እንደሚያውሉ ገልጿል።
በአማካይ 1.54 በመቶ ገቢያቸውን የለገሱ ሲሆን፣ ይህም በአውሮፓ ከሚታየው አማካይ 0.64 በመቶ በእጥፍ ይበልጣል።
ጥናቱ እንደሚያመለክተው፣ የአንድ ሀገር ሀብት እየጨመረ ሲሄድ የልግስና ደረጃው የመቀነስ አዝማሚያ ያሳያል። ከፍተኛ ገቢ ያላቸው አገሮች በአማካይ ከገቢያቸው 0.7 በመቶ ብቻ ሲለግሱ፣ እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ታዳጊ አፍሪካውያን አገሮች ግን ከፍተኛ የልግስና መጠን አሳይቷል ብሏል።
CapitalNews
