የሰሜን ኮሪያው ሁለንተናዊ መሪ ኪም ጆንግ ኡን ደቡብ ኮሪያ እና አጋሯ ዩናይትድ ስቴትስ ሀገራቸውን በነገር ከመተንኮስ አልፈው ወደ ጦርነት እንድትገባ እየገፋፉ እንደሆን በዚህ ከቀጠሉም ሰሜን ኮሪያ ራሷን ለመከላከል የኒውክሌር ጦር መሳሪያዋን ለመጠቀም እንደምትገደድ መናገራቸው ተሰማ ።
ኪም ይህን ያሉት ከአንድ ቀን በፊት ዩናይትድ ስቴትስ እና ደቡብ ኮሪያ ባህር ዳርቻ “የኡልቺ ፍሪደም ጋሻ ” የተሰኘው 21,000 የሁለቱ ሀገራት ወታደሮች የተሳተፉበት ለድንገተኛ አደጋ መከላከል ለማጥቃት ለመዘጋጀትና ሰሜን ኮሪያ የሚደርስባትን ስጋት በተሻለ ሁኔታ ለመቋቋም ያለመ አመታዊ መጠነ ሰፊ የጋራ ወታደራዊ ልምምድ መጀመራቸውን ተከትሎ ነዉ ።
ጉዳዩን አስመልክተው የተናገሩት የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ሀገራቸው የኒውክሌር ጦር መሳሪያዋን በፍጥነት ማስፋፋት እንዳለባት መናገራቸውን እና የአሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያ ወታደራዊ ልምምድ “ጦርነት ለመቀስቀስ ያላቸውን ፍላጎት በግልፅ የሚያሳይ ነው”ማለታቸውንና አፀፋ እንደምትሰጥ ማስጠንቀቃቸውን የመንግስት ሚዲያ ኬሲኤንኤ ማክሰኞ ዘግቧል።
ፒዮንግያንግ እንደዚህ አይነት ጠባ ጫሪነትና ለወረራ ቅድመ ዝግጂት የሆነ ልምምድ ሀገራቸው እንደማትታገስ የገለፁ ሲሆን በጦር መሣሪያ ሙከራዎች ምላሽ እንደምትሰጥም ገልፀዋል።
አክለዉም ልምምዶቹ “ለሰሜን ኮሪያ በጣም ጠላትነታቸዉን የሚያሳይ እና ግጭት የመቀጠል አላማቸው ግልፅ መግለጫ ነው ” በማለት የሰሜን ኮርና የባህር ኃይል መርከቦች በጎበኙበት ወቅት ተናግሯል ሲል የኬሲኤንኤ በእንግሊዘኛ ባወጣው ዘገባ አስነብቧል ።
አክለዉም በቅርቡ በአሜሪካ-ደቡብ ኮሪያ ልምምዶች “የኑክሌር ስልጠናን” ያካተተ መሆኑን በመጥቀስ ለደህንነትነታቸዉ አስጊ እንደሆነ በዝምታም እንደማያዩት ሰሜን የኒውክሌር ጦር መሳሪያዋን “በፍጥነት እንድታሳድግና እንድታስፋፋ” እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል ።
ከጋራ ልምምዱ ባሻገር የዩናይትድ ስቴትስ እና አጋሮቿ የሰሜን ኮሪያን የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ልማት ለመታገል በሚያደርጉት ጥረት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የደቡብ ኮሪያው ፕሬዝዳንት ሊ ጄ ሚዩንግ በዋሽንግተን ለስብሰባ ቀጠሮ መያዛቸውንም ከጀርባው የታቀደ ሴራ እንደሚኖረው አብራርተዋል ።
ሁለንተናዊ መሪዋ በተደጋጋሚ የኒውክሌር ጦር መሳሪያን መታጠቅና አቅምን ማደርጀት ማሻሻል ብቸኛ አማራጯ መሆኑን ሲናገሩ የሚደመጥላት ሰሜን ኮርያ እስካሁን እስከ 90 የሚደርሱ የኒውክሌር ጦር መሳሪያዎችን ለማምረት የሚያስችል አቅም እንዳላት
የአሜሪካ ሳይንቲስቶች ፌዴሬሽን ያረጋገጠ ሲሆን በሚቀጥለው ዓመት ጥቅምት ወር ላይ ሶስተኛውን 5,000 ቶን ቾ ሃይን-ክላስ አውዳሚ መሳርያ ለመገንባትና የጦር መርከቦቿንም የክሩዝ እና ፀረ-አየር ሚሳኤሎችን ለማስታጠቅ እየሰራች እንደምትገኝ በተደጋጋሚ ይነገራል ።
ለዘገባው ዋሽንግተን ፖስት lemonde international ሮይተርስን ተጠቅመናል ።
የኔታ ቲዩብ