የቀድሞው የሶርያ ፕሬዝዳንት በሽር አል-አሳድ በሌሉበት የእስር ማዘዣ ወጥቶባቸዋል

Date:

የሶርያ የሽግግር መንግስት የፍትህ ሚኒስቴር በቀድሞው የሶርያ ፕሬዝዳንት በሽር አል-አሳድ ላይ በሌሉበት የእስር ማዘዣ መውጣቱን አስታዉቋል።

ክሶቹም አስቀድሞ የታቀደ ግድያ፣ ማሰቃየት እና የእርስ በርስ ጦርነት ለማነሳሳት የታሰቡ ድርጊቶችን ያካትታሉ።

የቀድሞዉ ፕሬዝዳንት በተገኙበት ቦታ ሁሉ እንዲታሰሩ እና በተለየ የማቆያ ስፍራ እንዲቀመጡ አግባብነት ላላቸው የጸጥታ አካላት ጥሪ የቀረበ ሲሆን፤ የታጠቁ ኃይሎችም ትዕዛዙን እንዲፈጽሙ ታዘዋል።

የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች ከአሳድ የስልጣን ዘመን ጋር የተያያዙ ከባድ ጥሰቶችን ለረጅም ጊዜ ሲመዘግቡ ቆይተዋል፡፡

የዘፈቀደ የአየር ጥቃቶችን፣ የኬሚካል ጦር መሳሪያዎችን መጠቀም፣ የዘፈቀደ እስራቶችን፣ ወደ ሞት የሚያደርሱ ማሰቃየቶችን እና የጅምላ ግድያዎችን የሚያካትቱ ከባድ ወንጀሎችን መመዝገባቸዉ ተገልጿል፡፡

እነዚህ ጉዳዮች በዓለም አቀፍ ደረጃ እንደ ስልታዊ እና የጦር ወንጀሎች እንዲሁም በሰብዓዊነት ላይ የተፈጸሙ ወንጀሎች ተብለው ተገልጸዋል።

ከቀድሞዉ ፕሬዝዳንት በተጨማሪ የእስር ማዘዣዎቹ በአሳድ ወንድም ማኸር፣በከፍተኛ የጸጥታ ባለስልጣናት አሊ ማምሉክ እና አሊ አዩብ ላይም ወጥተዋል።

የመብት ቡድኖች ይህንን ሂደት በሶርያ የቅርብ ጊዜ ታሪክ ዉስጥ ግልጸኝነት እና ተጠያቂነትን ለማስፈን የተጀመረ አስፈላጊ እርምጃ ነዉ ብለዉታል፡፡

የሶርያ የፍትህ ሚኒስቴር የእስር ማዘዣውን ለመፈጸም ይፋዊ የጊዜ ሰሌዳ ያላስቀመጠ ሲሆን፤ ጉዳዩ ለተጨማሪ የህግ ሂደቶች ክፍት ሆኖ ይቆያል ብሏል እንደ አርቲ ኒዉስ ዘገባ።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ4.2 ሚሊዮን በላይ ሠራተኞች ይፈለጋሉ

በኢትዮጵያ ከ4.2 ሚሊዮን በላይ ክፍት የመንግሥት የሥራ መደቦች መኖራቸውንና...

አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የሂሳብ መዝገብ ሪፖርትን እስከ ነገ በቅጣት እንደሚቀበል አስታወቀ

  የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ዓመታዊ የግብር ግዴታቸውን ያልተወጡ ግብር...

ፈንታዬ በላይነህ የቦስተን ግማሽ ማራቶንን ለሦስተኛ ተከታታይ ጊዜ አሸነፈች

በ2026 የቦስተን ግማሽ ማራቶን ውድድር በሴቶች ምድብ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት...