የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ በዋሽንግተን ከትራምፕ ጋር ቆይታ አድርገው ከጨረሱ በኋላ ስለ ፑቲን አስተያየት ሰጥተዋል ተባለ።
ፑቲን እንደሚጠሉኝ አውቃለሁ የኔም ስሜት እንደዛው ተመሳሳይ ነው እጠላቸዋለሁ ሲሉ ለሪፖርተሮች ተናግረዋል።
ዘለንስኪ አሁን ላይ ጦርነቱ ባለበት ቆሞ ተኩስ አቁም እንዲረግ ለትራምፕ ጥሪ ማቅረባቸውም ተመላክቷል።
በኋይት ሀውስ ቆይታቸው ብዙም ደስተኛ ያልሆኑት ዘለንስኪ፣ ለአውሮፓ ወዳጆቻቸው ከትራምፕ ጋር የነበራቸውን ሁኔታ አሳውቀዋል ተብሏል።
የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ኬር ስታርመር ለዩክሬን ሰብአዊ እርዳታ እንደሚያቀርቡ ቃል ገብተዋል።
ትራምፕ እንደጋዛው ሁሉ የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነትንም እንዲያስቆሙ ስታርመር ጠይቀዋል።
ታይምስ ኦፍ ኢንዲ እና አር ቲ ኒውስ እንዳስነበቡት #NBCEthiopia