በተለይ ባለፉት 6 ወራት ሲመረምራቸው የነበሩ ቅሬታዎች ከ5 ዓመታት በላይ ተከማችተው ከነበሩ በርካታ ቅሬታዎች መካከል 25ቱን ሲሆን ከዚህም ውስጥ 21ዱ የህክምና ስህተት መሆናቸው ሲረጋገጥ 4ቱ ስህተት አለመሆናቸውን አረጋግጠናል ያሉን በባልስልጣኑ የህግ፤ የጤና ባለሙያዎችና ስነ ምግባር ክትትል ዳይሬክተር የሆኑት አቶ መትከል ገብረመድህን ናቸው፡፡
ከተፈፀሙት የህክምና ስህተቶች የሚበዙት በወሊድ ወቅት በሚደረግ የሪፈራል ህክምና ወቅት በህፃናትና በእናቶች ላይ የደረሱ ናቸው ያሉት አቶ መትከል፤ የተለያዩ ብለው ያለፏቸው ጉዳቶች ደርሰዋል ብለዋል፤ ነገር ግን ሞት የተከሰተባቸው እንዳልሆኑ ጠቁመዋል፡፡
በባለስልጣኑ ስር ያለው ይህንን ጉዳይ የሚመለከተው የስነ ምግባር ኮሚቴ ከፍተኛ የአካል ጉዳትና ሞት የሚያስከትል የህክምና ስህተት ተፈፅሞ ቢያገኝ እንኳን በባለሙያዎቹ ላይ ሊጥል የሚችለው ከፍተኛው ቅጣት ከሙያው ማሰናበት ነው የሚሉት ሃላፊው፤ የቅሬታ አቅራቢው ቀጣዩ እርምጃ ከእኛ የሚያገኘውን የቅጣት ወረቀት በመያዝና ወደ ህግ በመሄድ ክስ መመስረት ነው ሲሉም ጠቅሰዋል፡፡
የህክምና ስህተት ተፈፅሞብናል የሚሉ ክሶች ለዓመታት ሲደርሱት እንደነበር የነገረን የአዲስ አበባ ምግብና መድሃኒት ባለስልጣን በተለይ ከ2007 ዓ.ም ጀምሮ እየደረሱት አንድም ጊዜ ውሳኔ ሳይሰጥባቸው ለ10ዓመት የተከማቹ ከ3መቶ በላይ የቅሬታ መዝገቦች እንደነበሩ ጠቅሰዋል።
መስሪያ ቤታቸው ነበሩበት የባለሙያ እጥረትና ሌሎችም ችግሮች ለሚቀርቡ አቤቱታዎች ምላች ሳይሰጥ ቢቆይም ባለፈው ዓመት ተከማችተው ከነበሩት ከ3መቶ በላይ መዝገቦች ለ270ዎቹ ውሳኔ ሰጥቷል ብለዋል።
በዚህ ዓመትም ባሉት በቀሪዎቹ 6 ወራት የሚታዩ 45 ቅሬታዎች አሉ፤ እነዚህም በቀሪዎቹ የዓመቱ ጊዜያት እልባት ይሰጣቸዋል መባሉን ሰምተናል፡፡
ከሸገርን 102.1
