የእንግሊዝ የጤና ባለስልጣናት Wegovy እና Ozempic የተባሉ የክብደት መቀነሻ መርፌዎችን በሚወስዱ ሰዎች ላይ ከፍተኛ የጤና ስጋት መኖሩን አስጠነቀቁ።
ችግሩ፦ “ሴማግሉታይድ” የተባለውን ንጥረ ነገር የያዙ እነዚህ መድሃኒቶች NAION ለተባለና ድንገተኛ የአይን ብርሃን ማጣትን ለሚያስከትል “የአይን ስትሮክ” ሊዳርጉ ይችላሉ።
ምልክቱ፦ መድሃኒቱን የሚወስዱ ሰዎች ማንኛውም የዕይታ ለውጥ ካጋጠማቸው በአስቸኳይ ወደ ህክምና መሄድ እንዳለባቸው የእንግሊዝ የጤና ምርቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ (MHRA) አሳስቧል።
ውሳኔው፦ ቀደም ሲል አምራቹ ድርጅት (Novo Nordisk) ይህንን ችግር ባይቀበልም፣ አሁን ግን የጤና ባለስልጣናት ጉዳቱን በይፋ አረጋግጠዋል።
