በኢትዮጵያ እና በኬንያ ድንበር የሚደረግ ንግድ በገንዘብ መጠን ተገደበ

Date:

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር በኢትዮጵያ እና በኬንያ ድንበር የሚከናወነውን የንግድ ልውውጥ ህጋዊ ለማድረግ እና ለማስተካከል የሚያስችል አዲስ መመሪያ ተግባራዊ ማድረጉን አስታውቋል።

የኢትዮጵያ እና የኬንያ የጠረፍ ንግድ መመሪያ 1144/2018 ፣ በድንበር አካባቢ የሚኖሩ ማህበረሰቦች መሰረታዊ የፍጆታ ዕቃዎችን በህጋዊ መንገድ እንዲያገኙ ለማስቻል እና ከሀገሪቱ ዋና የንግድ ማዕከላት ርቀው ለሚኖሩ ነዋሪዎች የሚፈጠረውን የምርት እጥረት ለመቅረፍ ያለመ ነው።

ሚኒስትሩ እንደገለፀዉ ፤ የመመሪያዉ ዋና ትኩረት አነስተኛ የድንበር ንግድን ማደራጀት እና መደበኛ ያልሆነውን የንግድ እንቅስቃሴ ወደ ህጋዊ ሥርዓት ማስገባት እንደሆነ አብራርቷል።

በዚህም መሰረት አዲስ የገንዘብ እና የጉዞ ገደቦች ተቀምጠዋል፤ አንደኛው ነጋዴው በወር የሚገበያይባቸው ዕቃዎች ጠቅላላ ዋጋ ከ1,000 የአሜሪካ ዶላር ወይም ወደ 155,000 ብር መብለጥ እንደሌለበት ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ ብቁ የሆኑ ነጋዴዎች በወር ከፍተኛው አራት ጊዜ ብቻ የድንበር ተሻጋሪ ንግድ ማካሄድ እንደሚችሉ የሚደነግግ ነው።

“የድንበር አካባቢ” ተብሎ የተወሰነውም ከኢትዮጵያ በኩል 50 ኪሎ ሜትር እና ከኬንያ በኩል 100 ኪሎ ሜትር ርቀት ባለው ዞን ውስጥ የሚኖሩ ነዋሪዎችን ነው።

ለዚህ ፕሮግራም ብቁ ለመሆን ነጋዴዎች በተጠቀሰው የድንበር አካባቢ በቋሚነት የሚኖሩ የኢትዮጵያ ዜጎች መሆን እና በአካባቢው አስተዳደር አካላት መመረጥ ይጠበቅባቸዋል።

ከአምስት ቀናት በፊት የፀደቀው መመሪያው ለንግድ እንቅስቃሴ የሚፈቀዱ 50 ዓይነት የዕቃ አይነቶች እንዳሉት በዝርዝር አስቀምጧል። ከእነዚህም መካከል ግብርና ምርቶች፣ ከብቶች፣ ጨርቃ ጨርቅ እና የቤት ውስጥ ንፅህና መጠበቂያዎች ይገኙበታል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በኬንያ 190 ሕፃናትን በረሃብ በመግደል የ200 ዓመት እስር የተፈረደበት ‘ፓስተር’

በኬንያ “የዓለም ፍፃሜ ደርሷል” በሚል 190 ሕፃናት እና አንድ...

የኢትዮጵያ የጤና ሉዓላዊነት ጥረቶች ለአፍሪካ ሀገራት ተምሳሌት ናቸው

ኢትዮጵያ የጤና ሉዓላዊነቷን ለማረጋገጥ እያከናወነቻቸው ያሉ ተግባራት ለሌሎች የአፍሪካ...

35ኛው ዓለም አቀፍ የአካል ጉዳተኞች ቀን በአርባምንጭ ይከበራል

35ኛው ዓለም አቀፍ የአካል ጉዳተኞች ቀን ከህዳር 25 እስከ...

ቤተሰብን ማጠናከር ለሕጻናት ምቹ አፍሪካ መገንባት መሠረት ነው

የአፍሪካ የሕጻናት ፖሊሲ ፎረም ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ፣...