አሐዱ ባንክ ያልተጣራ 1.15 ቢሊዮን ብር ትርፍ አስመዘገበ!

Date:

የተጠናቀቀው በጀት ዓመት በአሐዱ፡ባንክ ጉዞ ውስጥ ጉልህ ስፍራ የሚሰጠው የስኬት ምዕራፍ ነው። በዚህም መሠረት፡-

ከመጠባበቂያና ግብር በፊት አምና ካስመዘገበው ጠቅላላ ትርፍ የ94.2% ዕድገት በማስመዝገብ ብር 1.15 ቢሊዮን ያልተጣራ ትርፍ አስመዝግቧል፣

የባንኩ ጠቅላላ ገቢም ወደ ብር 3.2 ቢሊዮን ከፍ ያለ ሲሆን፤ ይህም የ52% ዕድገት አሳይቷል፣በበጀት ዓመቱ የባንኩ የተቀማጭ ገንዘብ መጠን ወደ ብር 10.5 ቢሊዮን ከፍ በማለት የ32% ዕድገትን አሳይቷል።

ባንኩ የ126 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ በበጀት ዓመቱ ያገኘ ሲሆን፤ ይህም ከአምናው ተመሣሣይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ58% ዕድገት ያመላክታል፣ የባንኩ ጠቅላላ ሀብት ከብር 10.05 ቢሊዮን ወደ ብር 14.21 ቢሊዮን ያደገ ሲሆን፤ ይህም የ41.39% ዕድገት የታየበት ነው፡፡

ባንኩ የደንበኞቹን ቁጥር ወደ 1.34 ሚሊዮን በማሳደግ መሠረቱን እያሰፋ ይገኛል፤ አሐዱ፡ባንክ በዋና ዋና መለኪያዎች የላቀ የፋይናንስ ዕድገት ማስመዝገብ ብቻ ሳይሆን ፤ የባንኩን የወደፊት ትልም የሚያሳዩ 2B+G+ 15 ወለል ትልቅ ህንጻ ባለቤት በመሆን እና ሁነኛ የዲጂታል ባንኪንግ መተግበሪያዎችን (አሐዱ ለኩሉ እና ማኅደርን) አበልጽጎ ለአገልግሎት ማዋል መቻሉ የበጀት ዓመቱ ተጨማሪ አንኳር ስኬቶች ናቸው፡፡

በአጠቃላይ፤ አሐዱ፡ባንክ እ.ኤ.አ. ሰኔ 30 የተጠናቀቀውን የ2025/26 በጀት ዓመት በአንፀባራቂ ስኬቶች ታጅቦ ማጠናቀቁን ማወቅ ተችሏል፡፡

ከብዙዎች ለብዙዎች

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በኢትዮጵያ 50 ሚሊዮን የሚገመቱ ዜጎች የንፁህ መጠጥ ውሃ እንደማያገኙ ተነገረ

በኢትዮጵያ የንጹህ መጠጥ ውሃ ተደራሽነትን በበቂ ሁኔታ ለማሳካት የሚያስችል...

ገዳ ባንክ ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ አተረፍኩ አለ

ይህም ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ113 በመቶ እድገት አሳይቷል ...

እስራኤል የኢራን ተደራዳሪዎችን ለመግደል እያሴረች እንደነበር ተዘገበ

አሜሪካና ኢራን ወሳኝ የሆነውን የተኩስ አቁም ስምምነት በደረሱበት እስራኤል...

ከኡጋንዳ ወደ ኢትዮጵያ የመጀመሪያው በፋብሪካ የተቀነባበረ  የበሬ ሥጋ ንግድ ተጀመረ

‘ራንቸርስ ፋይነስት’ የተባለው የኡጋንዳ የግል ሥጋ አቀናባሪ ኩባንያ፣ በየወሩ...