የሥርዓተ ቀብር መረጃ:-
የሰቲት ሁመራ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ሉቃስ ዛሬ ጥቅምት 11 ቀን 2019 ዓ.ም ከዚህ ዓለም ድካም ያረፉ ሲሆን ሥርዓተ ቀብራቸውን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ ።
የብፁዕ አቡነ ሉቃስ ሥርዓተ ፍትሐት ጥቅምት 11 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ከቅዱስ ሲኖዶስ መክፈቻ ሥርዓተ ጸሎት ጋር በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ መሪነት የሚከናወን ሲሆን ፤ የሌሊቱ ሥርዓተ ፍትሐት እና አደራረስ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የሚከናወን ይሆናል፡፡
የብፁዕ አቡነ ሉቃስ ግብዓተ መሬት ነገ ጥቅምት 12 ቀን 2019 ዓ.ም በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ከቅዳሴ በኋላ የሚፈጸም መሆኑን ቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት በላከልን መግለጫ አስታውቋል፡፡
