የኢትዮጵያ ህብረት ስራ ማህበራት አጠቃላይ ካፒታል ፈጣን ዕድገት አስመዝግቦ ከ100 ቢሊየን ብር በላይ መድረሱ ተገልጿል።
የኢትዮጵያ ህብረት ስራ ኮሚሽነር ጌትነት ታደሰ እንደተናገሩት ከሶስት ዓመት በፊት የነበረው አጠቃላይ የህብረት ስራ ማህበራት ካፒታል 30 ቢሊየን ብር አይሞላም ነበር።
በአሁኑ ወቅት ይህ አሃዝ ከ 100 ቢሊየን ብር በላይ መድረሱን ጠቁመው በአስር አመት ውስጥ 1 ትሪሊየን ብር ለማድረስ መታቀዱን ገልጸዋል።
የዕቅድ አፈጻጸሙ ጥሩ የሚባል ይሁን እንጂ አሁንም ሰፊ ስራዎች እንደሚቀሩት ኮሚሽነሩ ተናግረዋል።
ህብረት ስራ ኮሚሽን ባገኘው መረጃ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ከ 18 ሺህ በላይ የህብረት ስራ ማህበራት አሉ።
