ከዚህ ቀደም «የሰጎን ፖለቲካ»ን በመሳሰሉ መጻሕፍታቸው የሚታወቁት ዶ/ር አለማየሁ አረዳ፤ «ምሉዕነት፡ ምሉዕ ሕብረተሰብ የመገንባት ጥበብ» የተሰኘውን አዲስ መጽሐፋቸውን ቅዳሜ ጥቅምት 21 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ በአድዋ ድል መታሰቢያ አዳራሽ ያስመርቃሉ።
ደራሲው «ከኢትዮጵያ የበለጠ የጋራ አጀንዳ የለንምና ጥሪዬን አክብራችሁ እንድትገኙ ተስፋ አደርጋለሁ» ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።
ይህ መጽሐፍ የተሻለ ማኅበረሰብ ለመገንባት የሚረዱ ሐሳቦችን የያዘ ሲሆን፤ በምረቃው መርሃ ግብር ላይ ለመገኘት የሚፈልጉ ሁሉ ተጋብዘዋል።
