ዲቪ ሎተሪ 2027 ዳግም እንዳይከፈት በፍርድ ቤት ታገደ

Date:

የአሜሪካ የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት የዲቪ ሎተሪ 2027 ምዝገባ እንዲከፈት ተሰጥቶ የነበረውን የታችኛውን ፍርድ ቤት ውሳኔ በጊዜያዊነት አግዶታል።

በዚህም ምክንያት ቀደም ሲል ለነገ እንዲከፈት ታዞ የነበረው የሎተሪ ምዝገባ በተያዘለት ጊዜ አይጀምርም።

አጠቃላይ ክስተቱ ምን ነበር ?

1. የመጀመሪያው እግድ 👉 ታህሳስ 2025 የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር የዲቪ ፕሮግራምን በጊዜያዊነት አገደ።

2. የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ውሳኔ 👉ነሐሴ 2026 የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዲቪ ቪዛ መስጠትን ዳግም ማገዱን አስታወቀ።

3. የህግ ክስ መመሥረት 👉 ነሐሴ 2026 ሬድ ኢግል ላው (Red Eagle Law) የተሰኘው ህግ ተቋም ፕሮግራሙ እንዲከፈት በሚል መንግስትን ከሰሰ።

4. የታች ፍርድ ቤት ትዕዛዝ 👉 ጥቅምት 2026 የፌደራል ፍርድ ቤት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የDV-2027 ምዝገባን ዳግም እንዲከፍት አዘዘ።

5. የይግባኝ አቤቱታ እና ጊዜያዊ እግድ 👉 ጥቅምት 2026 የትራምፕ መንግስት አስተዳደር ይግባኝ በማለቱ፣ የሰበር ሰሚ ፍርድ ቤት የታችኛውን ፍርድ ቤት ውሳኔ በጊዜያዊነት አገደው።

የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቱ ውሳኔው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፕሮግራሙን ለማገድ አስተላፎት የነበረውን ውሳኔ ይደግፋል ማለት እንዳልሆነ ተገልጿል። ሆኖም ክሱን የመሠረተው ” ሬድ ኢግል ላው “የተሰኘው የህግ ድርጅት መንግሥት ምዝገባውን ዳግም እንዲከፍት ለማስገደድ የሚያስችል በቂ የሕግ መብት እንደሌለው ፍርድ ቤቱ አረጋግጧል።

ዲቪ ሎተሪ የተቋቋመው ወደ አሜሪካ የሚገቡ ስደተኞች ቁጥር አነስተኛ የሆኑ ሀገራትን ለመደገፍ እንጂ ለህግ ድርጅቶች ቢዝነስ ለመፍጠር አይደለም ሲሉ ዳኞቹ ገልፀዋል።

ውሳኔው ማንን ይነካል ? የዲቪ-2027 ምዝገባ እስከ ነገ ይከፈታል ብለው ይጠብቁ የነበሩ አመልካቾችን በሙሉ ይነካል።

አሁን በተላለፈው ውሳኔ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ምዝገባውን ነገ የመክፈት ግዴታ የለበትም።

የዲቪ-2027 ምዝገባ የወደፊት እጣ ፈንታ አሁንም በህግ ሂደት ውስጥ ያለ በመሆኑ ግልጽ አይደለም። የህግ ክርክሩ እስኪጠናቀቅ ድረስ ፕሮግራሙ እንደታገደ ይቆያል።

@tikvahethiopia

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ቢል ጌትስ ስለ AI አጠቃቀማችን ምን አሉ?

የማይክሮሶፍት መስራች ቢል ጌትስ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) እና ሮቦቶች...

የማይደበዝዝ የታሪክ አሻራ፤

አበበ ቢቂላና ማሞ ወልዴ በዓለም መድረክ ግዮን መጽሔት :-...

በብፁዕ አቡነ ሩፋኤል ለስድስት ወር በደብረ ሊባኖስ ገዳም እንዲቆዩ ተወሰነ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ...

የኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ለ100 ሴቶች ነፃ የጡትና የማህፀን በር ካንሰር ምርመራ ዕድል ፈጠረ

የኤካ ኮተቤ ሆስፒታል የጥቅምት ወር ዓለም አቀፍ የጡት ካንሰር...