ቢል ጌትስ ስለ AI አጠቃቀማችን ምን አሉ?

Date:

የማይክሮሶፍት መስራች ቢል ጌትስ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) እና ሮቦቶች የሰዎችን ሥራ የመተካት አቅማቸው እየጨመረ በመጣ ቁጥር፣ ሰዎች የቴክኖሎጂ አጠቃቀማቸውን በራሳቸው ፍላጎት ሊገድቡ እንደሚችሉ ገለጹ። እ.ኤ.አ. ኦክቶበር 22፣ 2026 በተለቀቀው የ’ዲኮደር’ ፖድካስት ቃለ-መጠይቅ ላይ እንደተናገሩት፣ ማህበረሰቡ እንደ አሚሽ  ማህበረሰብ ባህል ሁሉ የላቁ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ለተወሰኑ የሕይወት ክፍሎች ብቻ መጠቀም እንዳለበት አሳስበዋል።

ቢል ጌትስ እንዳብራሩት፣ AI አብዛኞቹን ሥራዎች ከሰዎች የተሻለ የመወጣት አቅም ቢኖረው እንኳ ማህበረሰቡ የተወሰኑ ተግባራትን ለሰዎች ብቻ ለማስቀረት መወሰን ይችላል። በተለይም እንደ ሕፃናትን መንከባከብ፣ ምግብ ማዘጋጀት፣ ጥበብ እና ስፖርት ያሉ ሰብዓዊ ንክኪ የሚሹ ሥራዎች በ AI እና በሮቦቶች ከመተካት ይልቅ በሰዎች እጅ እንዲቀጥሉ ማድረግ እንደሚቻል አመልክተዋል።

በተጨማሪም ይሄው የቴክኖሎጂ ዕድገት የሚያስከትለው የሽግግር ወቅት ቀላል እንደማይሆን ቢል ጌትስ አስጠንቅቀዋል። ይኸው የ20 ዓመታት የሽግግር ጊዜ አሸናፊዎችና ተሸናፊዎች የሚፈጠሩበት፣ እንዲሁም ከፍተኛ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መስተጓጎል የሚታይበት በመሆኑ ትልቅ ስጋት እንደሆነባቸው ገልጸዋል። ሆኖም ሁሉም ሰው ቴክኖሎጂን ውድቅ ያደርጋል ከማለት ይልቅ፣ ሰዎች በሕይወታቸው ውስጥ ምን ያህል የ AI ቴክኖሎጂን ማስገባት እንደሚፈልጉ የመምረጥ መብት ይኖራቸዋል ሲሉ ተከራክረዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ዲቪ ሎተሪ 2027 ዳግም እንዳይከፈት በፍርድ ቤት ታገደ

የአሜሪካ የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት የዲቪ ሎተሪ 2027 ምዝገባ...

የማይደበዝዝ የታሪክ አሻራ፤

አበበ ቢቂላና ማሞ ወልዴ በዓለም መድረክ ግዮን መጽሔት :-...

በብፁዕ አቡነ ሩፋኤል ለስድስት ወር በደብረ ሊባኖስ ገዳም እንዲቆዩ ተወሰነ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ...

የኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ለ100 ሴቶች ነፃ የጡትና የማህፀን በር ካንሰር ምርመራ ዕድል ፈጠረ

የኤካ ኮተቤ ሆስፒታል የጥቅምት ወር ዓለም አቀፍ የጡት ካንሰር...