በመላው ዓለም በእምነታቸው ምክንያት ስደትና መከራ የሚደርስባቸውን ክርስቲያኖች ለማሰብ የሚካሄደው ዓመታዊው የ”ቀይ ሳምንት” ዘመቻ በፓሪስ ከሚገኘው የኖትር ዳም ካቴድራል ጀምሮ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች በመካሄድ ላይ ይገኛል።
ከኅዳር 6 እስከ 13 በሚቆየው በዚህ ዘመቻ 130 ታዋቂ ካቴድራሎች እንዲሁም በሺዎች የሚቆጠሩ አብያተ ክርስቲያናት፣ ሐውልቶች እና የሕዝብ ሕንፃዎች በቀይ ብርሃን ይታያሉ።
እንደ አዘጋጆቹ ገለጻ ቀዩ ብርሃን ስለ ክርስቶስ ሲሉ ሕይወታቸውን የሰጡ ሰማዕታትን ደም የሚወክል ሲሆን በሳምንቱ ውስጥም በተለያዩ ስፍራዎች የጸሎት ሥነ-ሥርዓቶች እና ሕዝባዊ ስብሰባዎች ለማካሄድ በዓለም ዙሪያ ከመቶ ሺዎች በላይ የሚሆኑ ሰዎች ይሳተፉበታል ተብሎ ይጠበቃል።
ዘመቻውን ከተቀላቀሉት የፈረንሳይ ዋና ከተማ አንዱ የሆነው የኖትር ዳም ካቴድራል ባወጣው መግለጫ፣ መርሐ-ግብሩ በስደት እና በመከራ ላይ ባሉ ክርስቲያኖች ዙሪያ ያለውን ዝምታ ለመስበር እና ዓለም እንዳልረሳቸው ለማረጋገጥ ያለመ መሆኑን አሳውቋል።
መረጃው የ Christian devotion ነው
