አቶ ደመቀ መኮንን በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ የሥነ-ምግብ ማሻሻያ ዓለም አቀፍ ንቅናቄ የመሪዎች ቡድን (SUN) አባል ሆነው ተሾሙ።
ዋና ጸሐፊው እ.ኤ.አ. ህዳር 17 ቀን 2026 በጻፉት ደብዳቤ፣ ሹመቱ አቶ ደመቀ የምግብ ዋስትናንና ሥነ-ምግብን ለማሻሻል ላሳዩት ቁርጠኝነት የተሰጠ እውቅና መሆኑን ገልጸዋል። የአባልነት ጊዜያቸውም ከህዳር 1 ቀን 2026 እስከ ታህሳስ 31 ቀን 2028 ይቆያል።
ለ67 አባል ሀገራትና ለ4 የሕንድ ግዛቶች ድጋፍ የሚያደርገው የመሪዎች ቡድን፣ በ2026–2030 የሥነ-ምግብ ማሻሻያ ማዕቀፍ ትግበራ ወቅት በምግብ ሥርዓት ሽግግር፣ በአየር ንብረት እርምጃና በግጭት ለተጎዱ ሀገራት ትኩረት በማድረግ ስትራቴጂካዊ መሪነት ይሰጣል።
አንቶኒዮ ጉቴሬዝ የአቶ ደመቀ መኮንን ልምድና አመራር ለንቅናቄው ግቦች ስኬት የላቀ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።
