በ2026 የላ ቪዳ (La Vida) ዓለም አቀፍ የፓስፖርት ደረጃ መለኪያ መሠረት፣ የደቡብ አፍሪካ ፓስፖርት ከሶማሊያ፣ ከካዛኪስታን፣ ከሩሲያ እና ከሌሎች 115 ሀገራት ፓስፖርቶች በታች በመቀመጥ ከ199 ሀገራት 119ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
ወደ 227 የጉዞ መዳረሻዎች ያለውን ተደራሽነት በሚመዝነው በዚህ መለኪያ፣ የደቡብ አፍሪካ ፓስፖርት ለዓለም አቀፍ ጉዞ፣ ንግድና ኢኮኖሚያዊ ተደራሽነት ያለው ውስንነት ተመላክቷል።
የፓስፖርቱ ደረጃ ዝቅ ማለቱ የሀገሪቱ ዜጎች፣ ነጋዴዎችና ባለሀብቶች ወደ ዓለም አቀፍ የንግድና ኢኮኖሚ ማዕከላት ያለ ቅድመ ቪዛ ለመጓዝ የሚያጋጥማቸውን እንቅፋት ያሳያል።
በዚሁ መለኪያ የኢትዮጵያ ፓስፖርት ከ199 ሀገራት 183ኛ ደረጃ ላይ መቀመጡ ተገልጿል።
