በድንገት ከዚህ ዓለም የተለየው የአርቲስት ሚኪያስ ቸርነት የቀብር ሥነ ሥርዓት ነገ ህዳር 14 ቀን 2019 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡00 ሰዓት በአዲስ አበባ በመንበረ ጽባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤተ ክርስቲያን እንደሚፈጸም ቤተሰቦቹ አስታወቁ።
ከቀብሩ ሥነ ሥርዓት አስቀድሞ ከረፋዱ 5:00 ሰዓት ጀምሮ በቃሊቲ በሚገኘው መኖሪያ ቤቱ የሽኝት ሥነ ሥርዓት ይካሄዳል።
በተጨማሪም በቤት ለቅሶ ለመገኘት ለሚፈልጉ ወገኖች፣ ቤተሰቦቹ ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን ፊት ለፊት፣ ወደ ገላን በሚወስደው መንገድ ሁለተኛ ቅያስ ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል።
የቤት ለቅሶ አድራሻ፦
በGoogle Maps አድራሻውን ይመልከቱ https://maps.google.com/?q=8.884331,38.773212
ለቤተሰቦቹ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹና ለመላው የጥበብ ቤተሰብ መጽናናቱን ይስጥ። ነፍሱን በገነት ያኑር!
