የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬስ፣ የሰው ሰራሽ አስተውሎት አጠቃቀም ሊያስከትላቸው የሚችሉ ስጋቶችን ለመቆጣጠር ሀገራት በጋራ እንዲሠሩና የተቀናጀ እርምጃ እንዲወስዱ ጥሪ አቅርበዋል።
ዋና ፀሐፊው፣ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ እየጠነከረና በስፋት እየተስፋፋ በመምጣቱ ከአጠቃቀሙ ጋር የተያያዙ ስጋቶችም እየጨመሩ መምጣታቸውን ገልጸዋል።
ቴክኖሎጂው በጤና፣ በትምህርት፣ በሳይንስና በልማት ዘርፎች አዳዲስ ዕድሎችን እየፈጠረ ቢሆንም፣ የሳይበር ጥቃቶችንና የዲጂታል ሥርዓቶች መቋረጥን ጨምሮ ሌሎች ተግዳሮቶችን ሊያስከትል እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።
አንቶኒዮ ጉቴሬስ፣ እያንዳንዱ ሀገር የሰው ሰራሽ አስተውሎትን በደህንነትና በኃላፊነት ለመጠቀም የሚያስችሉ አቅሞችን እንዲያዳብር አሳስበው፣ በሀገራት መካከል ያለውን የቴክኖሎጂና የአቅም ልዩነት ለመቀነስም የጋራ ጥረት እንዲደረግ ጠይቀዋል
