ነቢዩ ሲራክ
– ሕዝብን ከመንግሥት የለዬ ደጉ ወገን
– በአደጋ ስጋት ተከቦ እንግዳ ስቆ መቀበል
የሱዳን ሕዝቦች የክፉ ጊዜ መሸሸጊያ፣ መሻገሪያ ሆነውናልና እንወዳቸዋለን። ሱዳናውያን ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ሲሰደዱ እንደ ሁለተኛ ሀገራቸው አቅፈው ደግፈው ለተሻለ ህይዎት አብቅተዋቸዋል ። በአረብ ሀገሩ ስደትም ሱዳናዊ ወዳጅ ጓደኛ፣ የስራ ባልደረቦቸ ሆነው ኑሮን በፍቅር ገፍተናል። ሱዳኖች አብልተው አጠጥተው የጠገብክ አይመስላቸውም። ደጎች አይገልጻቸውም …
ሱዳኖች ለእኔ ከኩታ ገጠም ጎረቤትነት ባለፈ ልዩ ወንድምቸ እንደሆኑ ይሸማኛል ። በፍቅር እወዳቸዋለሁ። አከብራቸዋለሁ
ክፉው ስደት…
አፈንዲ ሙተቂ ካጋራን የስደተኛው ሱዳናዊና ቤተሰቡ ምስል የረዳሁት ብዙ እውነታ ነው ። እንዲህ ይላል “በሱዳን በሚካሄደው የእርስ በእርስ ጦርነት ሳቢያ የእርሱና የእህቶቹ ልጆች ህይወት ለአደጋ መጋለጡ አሳሰበው። በመሆኑም ልጆቹን ይዞ ከሀገር ለመሰደድ ወሰነ። በውሳኔው መሠረት ባለፈው ሳምንት ከካርቱም ተነሳ። ከጥቂት ቀናት ጉዞ በኋላ ወደ ኢትዮጵያዋ የጎንደር ከተማ ገባ። ከልጆቹ ጋር በሰላም ኢትዮጵያ መድረሱን ለማሳወቅ ሲል ይህንን ፎቶ ተነሳና “ልጆቹ በሰላም ኢትዮጵያ ደርሰዋል” ከሚል ጽሑፍ ጋር በፌስቡክ ግድግዳው ላይ ለጠፈው።” ይላል
ወገኔ ሕዝብና መንግሥት ይለያል‼
አዎ ሕዝብና መንግሥት ለየብቻ ናቸው። የሱዳንን መንግሥትን የሀገሬን ድንበር ደጋግሞ የጣሰ ፣ የአዋሳኝ ድንበር ነዋሪ ወገኖቻችን በግፍ ያዘፈናቀለ ፣ ፀረ -ኢትዮጵያ ሸማቂዎችን አስጠግቶ ወንድም ከወንድም ያጋደለን ፣ የአባይን ውሃ ሴራን ከግብጽ ጋር የዶለ ያስዶለተ ፣ የግብጵ እኩይ ሴራ አስፈጻሚ ተንከሲስ መንግሥት ቢኖር የሱዳን መንግሥት ነው። አዎ የሱዳንን መንግሥት ለጉርብትና የማይመች ነውና እልፍ አእላፎች መንግሥቱን እንደ ሕዝቡ አንወደውም።
አዎ ወገኔ ብልህ ነው ፣ መንግሥትን ከሕዝብ መለየት ያውቅበታል።
በስጋት ተከቦ ስቆ እንግዳ መቀበል
የሱዳን መንግሥት አሁን ድረስ ድንበሩን ገፍቶ ወስዶበት እያለ ኢትዮጵያዊው ወገኔ ሕዝብና መንግሥት ለይቶ ያውቃልና ድንበሩን ከፍቶ እጁን ዘርግቶ እንኳን ወደ ሁለተኛ ሀገራችሁ እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት እየተቀበላቸው ይገኛል ። ከሁሉም ገራሚው ጉዳይ ደግሞ እንግዳ ተቀባዩ ወገን በሀገር ውስጥ ፖለቲካ አቶን በስጋት እየለበለበ መሆኑ ነው … የህግ የበላይነት አደጋ ላይ ወደቆ እገታ ፣ ነፍስ ማጥፋት ፣ የመንገዶች መዘጋጋት ኑሮውን ያከፋው ደጉ የሀገሬ ሰው ሀገር ፈርሶት በእጁ ለወደቀው ለደጉ የሱዳን ስደተኛ ስቆ ተቀብሎ ሲያስተናግድ ስመለከት በሕዝቤን ደግነት እደመማለሁ።
አዎ ኢትዮጵያዊነት ድንቅ ነው ፤ በሀገር ከተማና ገጠሩ ኑሮ ውሎ አዳሩ በከፋ የስጋት አደጋ ተከቦ እንግዳውን ስቆ መቀበል ያውቅበታል። በፈተና ውስጥ እያለፍክ ደግነት የማይነጥፍብሀ ቸርና ደጉ ወገኔን ከልቤ አመሰግናለሁ፡፡
ሱዳናውያን ወገኖቸ ሆይ ወደ ሁለተኛ ሀገራችሁ ኢትዮጵያ በሰላም ገባችሁ!
—-///—-
ግብረ ሰዶማዊነት የርክሰት መንገድ ነው‼
– ግብረ ሰዶማዊነትን እቃወማለሁ‼
– የሕዝቡ ዝምታ ቁጣ አይደለምን‼
በሰዶማዊነት ትውልድ መበከል ሴራ…
ከሳምንታት በፊት የግብረ ሰዶማውያን መስፋፋት ሁሌም ከሚሳስባቸው ውስጥ የሚጠቀሱት ሊቀ ትጉሐን ደረጀ ነጋሽ ደጋግመው የነገሩን የግብረ ሰዶማውያን መስፋፋት እውነት በአንድ ታዋቂ ሆቴል ስልጠና እየተሰጠ ስለመሆኑ መረጃ ተሰራጭቶ ተመለከትኩ ። እያዘንኩ 😓 ስለ መረጃውን እውነታ መረጃ አገኝ ዘንድ የተባለው ሆቴን እንግዳ ሀኘ ባነፈንፍም በእጄ የገባ ሁነኛ ማረጋገጫ በማጣቴ ዝምታን መረጥኩ …
ትናንት አመሻሽ ላይ ግን ካንድ ሀገር ወገን ባህልና እምነቷን ከምትወድ እህት ብርቱ መረጃ ደረሰኝ ። መረጃው በሌላ በመሀል አዲስ አበባ በሚገኝ አንድ ትልቅ ሆቴል የግብረ ሰዶማውያን ጋብቻ ከወር በፊት በመፈጸሙን አስረጅ መረጃ ነበር ። በቦታው ከነበረ ታማኝ ምንጭ
የደረሰኝ መረጃ ሌላ ትውልድ የማጥፋት እና የመበከል ሴራ ህመም ሆኖኛልና እነሆ አቋም ሀሳቤን በአደባባይ ትረዱት
ዘንድ ሰዓቱ አሁን ነው …
ቀደም የሰው ዘር መገኛ ታሪኳ ፣ በራሷ ባህልና እምነት ቋንቋ ያላት እንግዳ ተቀባይ ሀገሬ በግብረ ሰዶማዊ ርክሰት እንድትበከል አልፈቅድም ። በየትኛወም እምነት በሐጢያትነቱ የሚወገዘውን እና ተቀባይነት በሌለው ግብረ ሰዶማዊነት ትውልድ መበከል መብት ነው ብዬ ከቶ አላምንም ። ግብረ ሰዶማዊነት ስልጣኔ እና እድገት ሳይሆን የፈጣሪን ትዕዛዛት መጣስ ነው ። ለእኔ ግብረ ሰዶማዊነትን ማስፋፋት የርክሰት ባህል ነው ። ግብረ ሰዶማዊነትን በኢትዮጵያ ማስፋፋት የኩሩ ባህልና ባለ ታሪክ ኩሩ ሕዝብን መናቅና ትውልድን የመበከል ሴራ ነው።
ጦርነት ቸነፈሩ ይበቃናል… ተውን‼
ዛሬም ተገቢ ባልሆነ የከፋ የእርስ በርስ ጦርነት ምድርነት ያልወጣችው ኢትዮጵያ ያለባትን ችግር የሚፈታ እንጅ የሐጢያት ፈተና የሚሆናት ግብረ ሰዶማዊነትን መሸከም አይቻላትም። ከዘላቂ ሰላም ይልክ በዘወትር ስጋትና የኑሮ ውድነት እየፈተነ ያለውን ሕዝብ ከችግሩ ሌላ ችግር አትሁኑቴ ። ክብሩን የሚመጥን ፣ ባህልና ታሪኩን የሚያስጠብቅ የሕዝብ አስተዳደር የለም በሚል ታብያችሁ የምትጓዙበት መንገድ የከበደ ዋጋ እንደሚያስከፍል አትዘንጉት።
በሚስጥር የጀመራችሁትን የግብረ ሰዶማውያን የርክሰት መንገድ ከልካይ አጥታቼሁ ዛሬ በግላጭ የኢትዮጵያን ምድር የሰዶምና ገሞራ ምድር ለማድረግ የምትጎዙበት የንቀት መንገድ አቁሙ‼ በአማኙ ሕዝብ ላይ በደልን ልትጭኑበት ዝምታው ቁጣ መሆኑን ከቶ ለሰከንድ ታክል አትጠራጠሩ‼
የሕዝቡ ዝምታ ቁጣ አይደለምን?!
እናንት የሕዝብ ዝምታው ቁጣ መሆኑ ያልገባችሁ እርኩሳን ሆይ, ተመከሩ ዛሬ ታብያችሁ የጀመራችሁት የግብረ ሰዶማዊ ማስፋፋት እንቅስቃሴ ለሀገረ ኢትዮጵያ አይመጥንም። ዳቦና ሰላም አጥቶ በችግር ኑሮን በተመስገን ለሚገፋ ሕዝብ ባህል ክብርና እምነቱን የሚጋፋ ሰዶማዊነትን መጫን አዋጭ አይደለም። ግብረ ሰዶማዊ እንቅስቃሴው በማንም ይመራ ፣ በማንም ይደገፍ ለኢትዮጵያ የማይበጅ የርክሰት መንገድ መሆኑን ተረዱት ።
እንደኔ እና መሰሎቸ ሀገር ወገኑን ለሚወድ አንድ ኩሩ ኢትዮጵያዊ የግብረ ሰዶማዊነት የርክሰት መንገድ መቃዎም የውዴታ ግዴታ ነው። ሰዶምን በእሳት ያነደዳት ግብረ ሰዶማዊነት ለኢትዮጵያ አይበጃትም። ኢትዮጰያን ለማርከስ የተነሳችሁ ከምንም በላይ ግን ፈጣሪን ፍሩ‼
የታበያችሁ ግብረ ሰዶማውያን ሆይ ዝም ያለው ሕዝብ ቁጣ ይግባችሁ። ታሪክ ፣ ባህልና እምነቱን የናቃችሁበት በድርጊታችሁ ተቆጥቶ ዝም ያለው ኩሩ ሕዝብ የተነሳ እንደሁ ወዮላችሁ‼
ዛሬም ሆነ ነገ … ግብረ ሰዶማዊነት በሀገሬ በኢቴዮጵያ ምድር እንዳይስፋፋ አጥብቄ እቃወማለሁ፣ አወግዘዋለሁ‼