ሩሲያው የሰራችው ለካንሰር ታማሚዎች ይሰጣል የተባለው የካንሰር ክትባት እ.አ.አ. በ2025 በመስከረም ወር ተመርቶ ለተጠቃሚዎች በነፃ ይደርሳል መባሉን ዘ ኢኮኖሚክ ታይምስ ይዞት የወጣው መረጃ ያመለክታል፡፡
ለአንድ የካንሰር ታማሚ የሚሰጠው ክትባት በግምት 2 ሺ 869 ዶላር ዋጋ የሚያወጣ ሲሆን፤ በልዩ ቁጥጥር ለዜጎች በነፃ ይሰራጫል ሲሉም የሩሲያ ጤና ሚኒስትር ተናግረዋል፡፡
ሩሲያ የሰራችው የካንሰር መከላከያ ክትባት በሰው ሰራሽ አስታውሎት በመታገዝ የሚሰጥ ሲሆን፤ የታማሚውን የመከላከል አቅም በማሳደግ ካንሰሩ በተማሚው ሰውነት በፍጥነት እንዳይሰራጭ የሚያደርግ ነው ተብሏል፡፡
የሩሲያ የጨራራ ሜዲካል ጥናትና ምርምር ማዕከል ኃላፊ አንድሪው ካፕሪን በበኩላቸው ይፋ የተደረገው ለታማሚዎች የሚሰጠው ክትባት ባህላዊ መድኃኒት አለመሆኑንም ተናግረዋል፡፡
በከፍተኛ ሁኔታ የሚሰራጨውን የካንሰር ዕጪ እድገትን በመቆጣጠር የሰው ልጆችን ሕይወት ይታደጋል የተባለለት የሩሲያ ግኝት በብዙዎች ታማሚዎች ተሞክሮ ተስፋ ሰጪ ውጤት እንደተገኘበት ኃላፊው ተናግረዋል፡፡
4 ሚሊዮን የሆኑ ሩሲያዊያን ከካንሰር ጋር እንደሚኖሩ የሚገልጸው መረጃዉ 625 ሺ ደግሞ በየዓመቱ ለካንሰር ተጋላጭ ስለ መሆናቸውም የሩሲያ ጤና ሚኒስቴርን ጠቅሶ ዘ ኢኮኖሚክ ታይምስ ዘግቧል።