ሰለ ሰራተኞች የሚከፈላቸው ደመወዝ

Date:


የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን አሁንም በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵዊያን ሰራተኞች የኑሮ ሁኔታ አሳሳቢነቱ ቀጥሏል ሲል አሳውቋል።
ኮንፌዴሬሽኑ ይህን ያለው በመጪው ሀሙስ በአለም አቀፍ ደረጃ ለ136ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ50ኛ ጊዜ የሚከበረውን የሰራተኞች ቀንን አስመልክቶ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ነው።
ኢሰማኮ “የዋጋ ግሽበት የደመወዝ ተከፋዩን የመግዛት አቅም በእጅጉ እንዳዳከመው ነው” ብሏል፡፡
ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል እስካሁን አለመወሰኑን ያስታወሰው ኮንፌዴሬሽኑ ሰራተኞች የሚከፈላቸው ደመወዝ አነስተኛ ሆኖ እያለ ከፍተኛ የገቢ ግብር ስለሚቆረጥባቸው መሰረታዊ ፍላጎታቸውን እንዳያሟሉ አድርጓቸዋል ብሏል፡፡
የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን ፕሬዘዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ “አንዳንድ አሰሪዎች፣ የማህበር መሪዎች ለአባሎቻቸው ስለቆሙ ወይም ለአባሎቻቸው መብት ስለተከራከሩ ብቻ ከስራ ይባረራሉ፣ ይዋከባሉ ወይም ራቅ ወዳለ ቦታ እንዲዘዋወሩ ይደረጋሉ” ብለዋል፡፡
“ኑሮ የከበዳቸውን ተቀጣሪ ሰራተኞችን በተመለከተ ከዚህ ቀደም ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የተላኩ ጥያቄዎችን በተመለከተ በተደረገው ውይይት ጥያቄያችን ተቀባይነት አግኝቶ ለሚመለከታቸው ሚኒስትሮች ተላልፎ ተሰጥቷቸዋል፤ ሆኖም የተወሰኑ ጥያቄዎች ምላሽ ያገኙ ቢሆንም መሰረታዊና ቁልፍ የሆኑ የሰራተኛ ጥያቄዎች አልተመለሱም” ሲሉም ገልጸዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብሮች

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 8ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ ይጀመራሉ። ዛሬ ሰባት...

ለዩክሬን ሰላም ‘በጣም ተቃርበናል’ ትራምፕ

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከዩክሬኑ ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ጋር በትናንትናው...

በዲማ የአለባበስ ቅጣት

በጋምቤላ ክልል ዲማ ከተማ ከባህል ውጪ በሆነ አለባበስ ምሽት...