በተፈናቃዮች ስም የፓለቲካ ትርፍ ለማግኘት የሚካሄደው እንቅስቃሴ ትክክል አይደለም

Date:

”  የፌደራል መንግስት ከፓለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ  የተሰረዘውን የህወሓት ቡድን የሚያካሂደው ፓለቲካዊ እንቅስቃሴ ህግና ስርዓት ማስያዝ ይገባዋል ” አለ ዴሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ (ስምረት) ፓርቲ።

ስምረት ፓርቲ በተፈናቃዮች ስም የፓለቲካ ትርፍ ለማግኘት የሚካሄደው እንቅስቃሴ ትክክል አይደለም ተቀባይነት የለውም ሲል አስታውቀዋል።

በእነ ሚንስትር አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ዴሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ ፓርቲ ይህንን ያለው በትግራይ ደረጃ ለ37ኛ ጊዜ የተከበረው የሰማእታት ቀን በማስመልከት ባወጣው ደርጅታዊ መግለጫ ነው።

ፓርቲው በመግለጫው ከግንቦት 2015 ዓ.ም ጀምሮ ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው ለመመለስ የተደረገውን እንቅስቃሴ ያደናቀፈው ” ኃላቀር ቡድን ” ሲል የገለፀው በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ነው ብሏል።

ቡድኑ ” ድርጅት ሳይድን የሚመለስ ተፈናቃይ የለም ፤ የጊዚያዊ አስተዳደር አመራሮች የትግራይ መሬት ሸጠዋል ” የሚሉና ልሎች በሬ ወለድ ወሬዎች በማስፋፋት የፌደራል መንግስትና ነባሩ ጊዚያዊ አስተዳደር ከግንቦት 2015 ዓ.ም ጀምረው የያዙት እቅድ ሙሉ በሙሉ እንዲደናቀፍ አደርገዋል ሲል ስምረት ህወሓትን ከሷል።

ስምረት ፓርቲ ” ቡድኑ ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው መመለስ ይቅርና ህወሓትን ከኢትዮጵያ የፓለቲካ ፓርቲዎች እንቅስቃሴ መሰረዝ መታደግ ያልቻለ አቅመ ቢስና መሰሪ ” ሲል የነ ደብረፅዮን (ዶ/ር) ህወሓትን አጣጥሎታል።

ስምረት ፤ ” ህገ-ወጥ ቡድኑ በቅርቡ ‘ የህዝብ ድጋፍ አለኝ ‘ ለማለት በማለም በተፈናቃዮች ስም ያካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ የተለመደው ማጭበርበርና ማታለያ እንደሆነ ህዝቡ በሚገባ ሊገነዘበው ይገባል ” ብሏል።

” ኋላቀር ቡድኑ ያለፈው ስህተት አልበቃ በሎት አሁንም ሌላ ፓለቲካዊ ክህደት እየፈፀመ ይገኛል ” ያለው ፓርቲው ” የትግራይ መሬት በወረራ ከያዘው የኤርትራ መንግስት የጀመረው ያልተቀደሰና ህገ-ወጥ ግንኙት ሌላ ዙር ግጭትና ጦርነት ከመቀስቀስ ያለፈ ውጤት እንደሌለው ሳይታለም የተፈታ ነው ”  ብሏል።

” ኋላቀር ቡድኑ ” ከኤርትራ መንግስት የጀመረውን ህገ-ወጥ ግንኙነት እንዲቆም የፌደራል መንግስት የሚገባውን ሃላፊነት  እንዲወጣ የጠየቀው ስምረት ” በአገራዊ ህጎች ከማንኛውም ፓለቲካዊ እንቅስቃሴ የተከለከለ ቡድን ከአፍራሽ ተግባሩ በማቆም ተጠያቂነት ማረጋገጥ ይገባል ” ሲል አክሏል።

ስምረት ፓርቲ የትግራይ መሰረታዊ ችግሮች እንዲፈቱና የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በሙሉነት እንዲተገበር ከፌደራል መንግስትና ከዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ተቀናጅቶ እንደሚሰራ ማስታወቁ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ የፓርቲው መግለጫ ጠቅሶ ዘግቧል።

@tikvahethiopia       

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ4.2 ሚሊዮን በላይ ሠራተኞች ይፈለጋሉ

በኢትዮጵያ ከ4.2 ሚሊዮን በላይ ክፍት የመንግሥት የሥራ መደቦች መኖራቸውንና...

አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የሂሳብ መዝገብ ሪፖርትን እስከ ነገ በቅጣት እንደሚቀበል አስታወቀ

  የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ዓመታዊ የግብር ግዴታቸውን ያልተወጡ ግብር...

ፈንታዬ በላይነህ የቦስተን ግማሽ ማራቶንን ለሦስተኛ ተከታታይ ጊዜ አሸነፈች

በ2026 የቦስተን ግማሽ ማራቶን ውድድር በሴቶች ምድብ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት...