ከ1 ሺህ 100 በላይ የቁጠባና ብድር ማኅበራትን ለማዋሃድ እየተሠራ ነው

Date:

የአዲስ አበባ ከተማ ህብረት ሥራ ኮሚሽን በከተማዋ የሚገኙ ከ1 ሺህ 100 በላይ የቁጠባና ብድር ማኅበራትን በማዋሃድ የፋይናንስና የብድር አቅማቸውን ለማጠናከር እንዲሁም በቴክኖሎጂ ለማዘመን እየሠራ መሆኑን ገለጸ።

የኮሚሽኑ የፋይናንስ ህብረት ሥራ ልማት ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ አክሊሉ፣ ማኅበራቱን ከማብዛት ይልቅ ውስንና ጠንካራ ማድረግ ተገቢ መሆኑን ጠቅሰው፣ በማዋሃድ የተሻለ የፋይናንስ አቅምና የብድር አቅርቦት እንዲኖራቸው እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል።

ማኅበራቱ በቴክኖሎጂ አጠቃቀም ከሌሎች የፋይናንስ ተቋማት አንጻር ወደኋላ የቀሩ መሆናቸውን በመጥቀስ፣ ይህንን ክፍተት ለመቅረፍና ማኅበራቱን በቴክኖሎጂ ለማዘመን ኮሚሽኑ በትኩረት እየሠራ መሆኑን አስታውቀዋል።

ማኅበራቱን ማዋሃድ የብድር አገልግሎትን ከማስፋፋት ባለፈ ለአባላት የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጡና በዘላቂነት እንዲጠናከሩ ወሳኝ መሆኑን ኮሚሽኑ ጠቁሟል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የቡሌ ሆራ መሶብ አንድ ማዕከል 54 የመንግሥት አገልግሎቶችን ለመስጠት ዝግጁ ሆነ

በደቡብ ኦሮሚያ ዞን ቡሌ ሆራ ወረዳ የተገነባው መሶብ አንድ...

13ኛው የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ሥነ ሥርዓት ኅዳር 12 ይካሄዳል

13ኛው የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ሥነ ሥርዓት ኅዳር 12 ይካሄዳል 13ኛው...

የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ ሰራተኞች ክስ ዳግም እንዲታይ ተወሰነ

ከሦስት ዓመት በላይ በፍርድ ቤቶች ሲከራከር የቆየው የተንዳሆ ስኳር...

በአራት ወራት ከ2,472 ኪ.ሜ በላይ የኤሌክትሪክ መስመር ግንባታና ማሻሻያ ተከናወነ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ አራት ወራት...