የትግራይ አባቶች የሲኖዶስን ውሳኔ ተቃወሙ

Date:

የትግራይ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አባቶች፣ በአወዛጋቢው ደቡባዊ ትግራይ በማይጨው አገረ ስብከት ሥር ሲተዳደሩ የነበሩት አላማጣ፣ ኦፍላ፣ ዛታ እና ጨርጨር ወረዳዎች እንዲኹም አላማጣና ኮረም ከተሞች ራሱን የቻለ አገረ ስብከት እንዲኾኑ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ሲኖዶስ በቅርቡ ውሳኔ ማሳለፉን መቃወማቸው ተሠምቷል።

አገረ ስብከት የሚቋቋመው ለዞኖች ብቻ መኾኑን የጠቀሱት የክልሉ አባቶች፤ ውሳኔው የአማራና የትግራይ ሕዝቦች ቅራኔ ውስጥ እንዲገቡ የሚያደርግ ነው በማለት ውድቅ. ማድረጋቸውን የዘገበው ድምጸ ወያኔ ነው።

የሲኖዶሱ ውሳኔ፣ የትግራይን ግዛታዊ አንድነት የሚጥስና የግዛት መስፋፋት ለማካሄድ የታለመ ነው በማለት የኃይማኖት አባቶቹ እንደፈረጁትም ተገልጧል።

የዋዜማ ራዲዮ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ4.2 ሚሊዮን በላይ ሠራተኞች ይፈለጋሉ

በኢትዮጵያ ከ4.2 ሚሊዮን በላይ ክፍት የመንግሥት የሥራ መደቦች መኖራቸውንና...

አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የሂሳብ መዝገብ ሪፖርትን እስከ ነገ በቅጣት እንደሚቀበል አስታወቀ

  የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ዓመታዊ የግብር ግዴታቸውን ያልተወጡ ግብር...

ፈንታዬ በላይነህ የቦስተን ግማሽ ማራቶንን ለሦስተኛ ተከታታይ ጊዜ አሸነፈች

በ2026 የቦስተን ግማሽ ማራቶን ውድድር በሴቶች ምድብ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት...