አትሌት ፋንታዬ በላይነህ ትናንት ምሽት የዙሪክ ዳይመንድ ሊግ ፍፃሜ በ3000 ሜትር ማሸነፏን ተከትሎ ለቶኪዮ የዓለም ሻምፒዮና በWild Card በቀጥታ ማለፏን አረጋግጣለች።
የዓለም አትሌቲክስ አዲስ ባወጣው ህግ መሰረት ቀደም ሲል ለሻምፒዮናው ሚኒማ ያላሟሉ ወይም ሚኒማ ኖሯቸው በሌሎች አትሌቶች በመበለጣቸው ምክንያት በሀገራቸው ብ/ቡድን መካተት ያልቻሉ አትሌቶች በዳይመንድ ሊጉ ፍፃሜ ካሸነፉ በቀጥታ በWild Card እንዲያልፉ ወስኗል።
ፋንታዬ በላይነህ የዛሬ ድሏን ተከትሎ የቶኪዮ ቲኬቷን መቁረጥ ችላለች። በዚህም መሰረት በዓለም ሻምፒዮናው በ5000 ሜትር ትወዳደራለች። ምክንያቱም በዓለም ሻምፒዮና የሴቶች 3000 ሜትር መሰናክል እንጂ የቀጥታ ውድድር የለም። በ5000 ሜትር የተሳታፊ አትሌቶቻችንም ቁጥር ወደ አራት ከፍ ብሎልናል።
አሁን ሁሉም ነገር ተጠናቅቋል…ሙሉ ትኩረታችን የቶኪዮ የዓለም ሻምፒዮና ይሆናል!!
መልካም ዕድል ለጀግኖች ለአትሌቶቻችን!!
ምስጋናው ታደሰ
