የክብደት መቀነሻ መርፌዎች ለድንገተኛ አይነ ስውርነት ሊዳርጉ እንደሚችሉ ተነገረ

Date:

​የእንግሊዝ የጤና ባለስልጣናት Wegovy እና Ozempic የተባሉ የክብደት መቀነሻ መርፌዎችን በሚወስዱ ሰዎች ላይ ከፍተኛ የጤና ስጋት መኖሩን አስጠነቀቁ።

​ችግሩ፦ “ሴማግሉታይድ”  የተባለውን ንጥረ ነገር የያዙ እነዚህ መድሃኒቶች NAION ለተባለና ድንገተኛ የአይን ብርሃን ማጣትን ለሚያስከትል “የአይን ስትሮክ” ሊዳርጉ ይችላሉ።

​ምልክቱ፦ መድሃኒቱን የሚወስዱ ሰዎች ማንኛውም የዕይታ ለውጥ ካጋጠማቸው በአስቸኳይ ወደ ህክምና መሄድ እንዳለባቸው የእንግሊዝ የጤና ምርቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ (MHRA) አሳስቧል።

​ውሳኔው፦ ቀደም ሲል አምራቹ ድርጅት (Novo Nordisk) ይህንን ችግር ባይቀበልም፣ አሁን ግን የጤና ባለስልጣናት ጉዳቱን በይፋ አረጋግጠዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ4.2 ሚሊዮን በላይ ሠራተኞች ይፈለጋሉ

በኢትዮጵያ ከ4.2 ሚሊዮን በላይ ክፍት የመንግሥት የሥራ መደቦች መኖራቸውንና...

አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የሂሳብ መዝገብ ሪፖርትን እስከ ነገ በቅጣት እንደሚቀበል አስታወቀ

  የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ዓመታዊ የግብር ግዴታቸውን ያልተወጡ ግብር...

ፈንታዬ በላይነህ የቦስተን ግማሽ ማራቶንን ለሦስተኛ ተከታታይ ጊዜ አሸነፈች

በ2026 የቦስተን ግማሽ ማራቶን ውድድር በሴቶች ምድብ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት...