ደቡብ ኦሮሚያ ዞን 3.2 ሚሊዮን ኩንታል ቡና ለመሰብሰብ አቅዷል

Date:

የደቡብ ኦሮሚያ ዞን በ2019 በጀት ዓመት የቡና ምርታማነትን በማሳደግ 3.2 ሚሊዮን ኩንታል ቡና ለመሰብሰብ እየሠራ መሆኑን አስታወቀ።

የዞኑ የግብርና ጽሕፈት ቤት ምክትል ኃላፊ ምህረት በለጠ እንደገለጹት፤ በመጀመሪያው ሩብ ዓመት 316 ሺህ ኩንታል ገደማ ቡና ተሰብስቧል። በበጀት ዓመቱም 119 ሺህ ቶን ቡና ለገበያ ለማቅረብ እየተሠራ ሲሆን፤ ከዚህ 55 ሺህ ቶኑ ለዓለም አቀፍ ገበያ የሚቀርብ ነው።

በዞኑ ከ46 ወረዳዎች 21ዱ ቡና አምራች ሲሆኑ፣ 250 ሺህ የሚጠጉ አርሶ አደሮች በቡና ልማት ተሰማርተዋል። ከዞኑ የግብርና መሬት 371 ሺህ ሄክታር በቡና ተክል መሸፈኑንም ኃላፊው ጠቁመዋል።

በቡና ምርታማነት ላይ ትኩረት በማድረግ የምርት ጥራትንና ዘላቂነትን ለማረጋገጥ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑ ተገልጿል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ነገ በፓርላማ ተገኝተው ማብራሪያ ይሰጣሉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመጪው ሐሙስ ህዳር 17...

ከፍተኛ የወጪ ንግድ ገቢ ያስመዘገቡ ድርጅቶች ተሸለሙ

በጥራጥሬና ቅባት እህሎች ዘርፍ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ገቢ ያስገኙ...

ዓለም አቀፉ ሽልማት ለጋዜጠኛ ይስሐቅ በላይ ተሰጠዉ

ዓለም አቀፉ ኦሎምፒክ ኮሚቴ (IOC) በ4ኛው የዓለም የወጣቶች ኦሎምፒክ...

የተመድ ዋና ፀሐፊ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ስጋቶችን ለመቆጣጠር ዓለም አቀፍ ትብብር ጠየቁ

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬስ፣ የሰው ሰራሽ...