ዲጂታል ፈጣሪዎች ግብር ይከፍላሉ

Date:

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የፌዴራል የገቢ ግብር ደንብን ለማሻሻል ያወጣው ደንብ ቁጥር 597/2019 በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ሥራ ላይ መዋሉን ዘግቧል። ደንቡ ግልጽነትንና አስተዳደራዊ ቅልጥፍናን ለማረጋገጥ እንዲሁም ከፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅ ጋር ለማጣጣም መውጣቱ ተገልጿል።

በአዲሱ ደንብ የዲጂታል ይዘት ፈጣሪዎችን ገቢና እንቅስቃሴ የሚመለከቱ ድንጋጌዎች ተካተዋል። በዚህም መሠረት በአንድ የግብር ዓመት ከይዘት ፈጠራ የሚገኘው ጠቅላላ ገቢ ከ50 ሺህ ብር በላይ የሆነ ማንኛውም ፈጣሪ የገቢ ግብር የመክፈል ግዴታ ይኖርበታል።

በዓመቱ የተገኘው ገቢ ከ50 ሺህ ብር የማይበልጥ ከሆነ፣ ከዚያ በፊት የተከፈለ ግብር ከወደፊት የግብር ግዴታ ጋር እንዲካካስ ወይም ተመላሽ እንዲደረግ ደንቡ ያዛል። የገቢዎች ሚኒስቴርም የገንዘብ የመግዛት አቅምን በመመልከት የ50 ሺህ ብር ገደቡን በመመሪያ ሊያሻሽል እንደሚችል ተጠቅሷል።

በኢትዮጵያ ነዋሪ የሆነ የዲጂታል ይዘት ፈጣሪ በይዘት ፈጠራው ለሚያገኘው ገቢ ግብር የመክፈል ግዴታ እንዳለበትም ደንቡ ያስቀምጣል። የዲጂታል መድረኩ አካውንት ከኢትዮጵያ ውጪ መከፈቱ ወይም ክፍያው በውጭ አገር ባንክ መፈጸሙ ከግብር ግዴታ ነፃ እንደማያደርግ በደንቡ ተገልጿል።

ለዲጂታል ይዘት ፈጣሪዎች ክፍያ የሚያመቻቹ ድረ ገጾች፣ የማኅበራዊ ሚዲያ መተግበሪያዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ መገበያያ መድረኮች፣ የቀጥታ ስርጭት አገልግሎቶችና የማስታወቂያ ድርጅቶች በኢትዮጵያ ነዋሪ የሆኑ ፈጣሪዎችን መረጃ ለታክስ ባለሥልጣኑ የማቅረብ ግዴታ ተጥሎባቸዋል።

መድረኮቹ የክፍያ ጥያቄ የቀረበበትን አድራሻ፣ የሲም ካርድ መረጃና የአይፒ አድራሻን መነሻ በማድረግ የፈጣሪዎችን ስም፣ አድራሻና የተከፈላቸውን ገንዘብ መጠን በየሩብ ዓመቱ ለታክስ ባለሥልጣኑ ማቅረብ አለባቸው።

በተጨማሪም የዲጂታል ይዘት ፈጣሪዎች የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የመያዝ፣ ገቢያቸውን የማሳወቅና በየሩብ ዓመቱ ግብር የመክፈል ግዴታ እንዳለባቸው ተደንግጓል።

የታክስ ባለሥልጣኑም የዲጂታል ይዘት ፈጣሪዎችን እንቅስቃሴ የመከታተል፣ ግብር የመክፈል ግዴታ ያለባቸውን የመለየትና ከሀገር ውስጥም ሆነ ከዓለም አቀፍ የዲጂታል መድረኮች ጋር በትብብር የመሥራት ኃላፊነት ተሰጥቶታል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ይድረስ ካገሬ ኢትዮጵያ የፌደራልና ክልሎች ባለስልጣናት!

ኢትዮጵያዊው ሊቅ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም በአንድ ወቅት ሚዲያ...

የኢትዮጵያ ከ 23ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ከሞሮኮ ጋር ያደረገውን የአፍሪካ ዋንጫ

የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ለ2027 የአፍሪካ ዋንጫ...

ማንችስተር ዩናይትድ አሰልጣኙን ማይክል ካሪክን አሰናበተ

የእንግሊዙ ማንችስተር ዩናይትድ ክለብ ዋና አሰልጣኙን ማይክል ካሪክን ከኃላፊነታቸው...

ኢትዮጵያ በCOP31 የደን ጥበቃና የአየር ንብረት ተግባር ላይ ጥሪ አቀረበች

ኢትዮጵያ በቱርክዬ አንታሊያ በተካሄደው የCOP31 መሪዎች ዝግጅት፣ “ደኖችና የአየር...