ህዝባዊ ተቃውሞ በዩክሬን

Date:


የፀረ-ሙስና ኤጀንሲዎችን የሚያዳክመው የዘለንስኪ አዲስ ህግ በኪየቭ፣ ሊቪቭ፣ ዲኒፕሮ እና ኦዴሳ ከተሞች ውስጥ ህዝባዊ ተቃውሞዎችን ቀስቅሷል፡፡

ፕሬዝደንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ የሀገሪቱን ገለልተኛ የፀረ-ሙስና ኤጀንሲዎች የዩክሬን ጠቅላይ አቃቤ ህግ ሙሉ ስልጣን የሚያስረክብ አወዛጋቢ ህግ ፈርመዋል።

ይህ ህዝባዊ ተቃውሞ እ.ኤ.አ. በ2022 የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት ወዲህ ትልቁን ፀረ-መንግስት ተቃውሞ አስነስቷል።

በብሔራዊ ፀረ-ሙስና ቢሮ (NABU) እና በልዩ ፀረ-ሙስና አቃቤ ህግ ቢሮ (SAPO) የሚመራውን ምርመራ ለመቆጣጠር እና ለመመደብ ለጠቅላይ አቃቤ ህግ ስልጣን ይሰጣል።

ብሔራዊ ፀረ-ሙስና ቢሮ (NABU) እና ልዩ ፀረ-ሙስና አቃቤ ህግ ቢሮ (SAPO) በዩክሬን ሙስናን ለማጥፋት የቆዩ ሁለት ቁልፍ ተቋማት ናቸው። እርምጃው እነዚህን ኤጀንሲዎች ነፃነታቸውን የሚገፍ እና ወደ ፖለቲካ መሳሪያነት የመቀየር ስጋት እንዳለው ተገልጿል።

NBC Ethiopia

russia

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የአርቲስት ነጻነት ወርቅነህ ስርዓተ ቀብር ተፈጸመ

የአርቲስት ነጻነት ወርቅነህ ስርዓተ ቀብር በመንበረ ጸባኦት ቅድስት...

በእስር ላይ የሚገኙት መምህርት መስከረም ዓይናቸው በጽኑ መታመሙን ጠበቃቸው ገለጹ

ከሁለት ዓመት በላይ በእስር ላይ የሚገኙት መምህርት መስከረም አበራ...

ንግድ ባንክ “ስታርፔይ” የተሰኘ አዲስ መተግበሪያ ይፋ አደረገ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዲጂታል ባንክ ሥርዓቱን ይበልጥ ዘመናዊና ቀልጣፋ...

በኢትዮጵያ በካንሰር ከሚያዙ ሕፃናት መካከል 75 በመቶ የሚሆኑት ህክምና አያገኙም

በኢትዮጵያ በየዓመቱ በካንሰር ከሚጠቁ ከ6 ሺህ እስከ 8 ሺህ...