ፍልውሃ እና ሶደሬ!

Date:

ከሐዉለት አህመድ

በቀደም ከብዙ ዓመታት በኋላ የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ሔጄ ነበር። ፍልውሃ ገና fresh የዩኒቨርሲቲ graduate ሆኜ በጠዋቱ የማውቀው ቦታ ነው። ምናልባት አጎንብሶ ከማንበብ ብዛት ሊሆን የሚችል የጀርባ ሕመም ስለነበረኝ ገና ሃያዎቹ መጀመሪያ ላይ ሳለሁ ለፊዚዮቴራፒ ህክምና በተደጋጋሚ ፍልውሃ እሔድ ነበር።

ያኔ 22 ብር የነበረው ሙሉ ሰውነት የመታሻ አገልግሎት (ግማሽ የሚባልም ነበር፤ በ 15 ብር) አሁን በየደረጃው 900 ብር፣ 1,200 ብር እና 2,500 ብር ሆኗል። የገንዘቡ ጭማሪ ይሁን። ይሁንና የመታሻ አገልግሎቱ የዛሬ 20 ዓመት ከነበረው ምንም አለመሻሻሉ ብቻ ሳይሆን እንዲያውም የቀነሰ ሆኖ ነው ያገኘሁት።

ሌላው ሶደሬ ነው። የሶደሬማ ምኑ ይነሳል? ሶደሬን የመሰለ የፈውስ ቦታ ማስተዳደር የመቻል አቅማቸው ሳይረጋገጥ ለሆኑ ‘ባለሃብቶች’ ሲሸጥ እና ከዚያ በኋላ ሲዝረከረክ፣ ተመጣጣኝ የነበረው ዋጋ ውድ እንዲሆን ሲደረግ፣ በኋላም በ ‘ጸጥታ መደፍረስ ምክንያት’ ከጨዋታ ውጪ ሲሆን … ብቻ ያሳዝናል።

እነዚህ ሁለት ሥፍራዎች የመዝናኛ ወይም ቅንጦት ሥፍራዎች የሚመስሉት ሰው አይጠፋም። NO! በዋናነት ‘የተፈጥሮ ሕክምና ማዕከላት’ ናቸው። እነዚህ ገራሚ ተፈጥሮአዊ ህክምና ማዕከላት ድክም ብለው ማየት ያሳዝናል።

ዕድሜአቸው ዘለግ ያሉ ተቋማት የሉንም። 100 ዓመት ወደኋላ ብንሔድ የምናገኛቸው በጣም ጥቂት ናቸው። የአንዳንድ አገራት ተቋም (instituition) አጠባበቅ ገራሚ ነው።

ለምሳሌ ኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ከ900 ዓመታት በላይ አስቆጥሯል። አንዳንድ ግዙፍ መካከለኛ እና አነስተኛ የቢዝነስ ተቋማት ሳይቀሩ ከትውልድ ትውልድ እየተሸጋገሩ Since 1713 ወይም 1612 ወይም 1811… የሚል ሳይ ቅናት ብጤ ሽው ይልብኛል።

የተቋም ዕድሜ ዘለግ ማለት ለቁጥር ብዛት አይደለም። ከዚያ ይልቅ፦
– በብዙ ሰው ህይወት ውስጥ የትዝታ ማኅደርነታቸው
– በአንድ አገር ታሪክ ውስጥ ያላቸው ሥፍራ የጎላ መሆን
– የእውቀት እና የልምድ ልውውጥ ቦታ መሆናቸው
– መታወቂያ (national identity) ሆነው ከፊት መቀመጣቸው
– ያለፈውን ከሚመጣው ትውልድ ማስተሳሰራቸው
– የብዙ ዓመታት ፈተናን በጽናት መቋቋማቸው ለዜጎች የሚሰጠው መተማመን የመሣሠሉት በምንም አይተኬ ጥቅሞቻቸውን ማንሳት ይቻላል።

ሁለቱ ማዕከላት እንደምሳሌ ተነሱ እንጂ እንዲሁ ቀስ እያሉ እየከሰሙ ያሉ ተቋሞቻችን ቁጥር ትንሽ የሚባል አይደለም።

የታዳጊ አገራት መሪዎች ከሚያስገርሙን ባሕሪዎቻቸው አንዱ ከእነርሱ በፊት የነበሩት መሪዎች ያቋቋሟቸውን ተቋማት ችላ በማለት እንዲዳከሙ የመተው ወይም እስከናካቴው እንዲጠፉ የማድረግ ነገራቸው እና የራሳቸውን ሥም የሚያስነሱላቸው አዳዲስ ነገሮችን ከ scratch መጀመራቸው ነው።

የቀደመው ቢጠናከር ምን ችግር አለው? መጪውም እንደገና አሁን ያለውን እንደሚያዳክም እየታወቀ ከዜሮ መጀመር ምን ጥቅም? ‘ያለውንም ማጠናከር፤ አዳዲስም መጀመር’ ቢሆን አይሻልም ወይ? እንዲህ ቢቀጥል የሚሄዱትም ሆነ ገና የሚመጡት መሪዎች አሻራ እንደተጠበቀ የሚቀጥል ይመስለኛል።

አለዚያ Since….የሚል ዘመናትን የሚሻገር ተቋም እንደናፈቀን መቅረቱ ነው።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እግዚአብሔር የሰጠኝን ተልዕኮዎች ፈጽሜያለሁ የአዛዥነት ዘመኔ እያበቃ ነው

የኡጋንዳ የመከላከያ ኃይሎች አዛዥ (CDF) ጄነራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ ከወታደራዊ...

አሐዱ ባንክ 1ነጥብ 07 ቢሊዮን ብር አተረፈ

ባንኩ በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር...

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...

የተጀመሩ የትምህርት ሪፎርሞችን በጽኑ መሠረት ላይ ለማቆም በቁርጠኝነት መስራት ይገባል

የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮችና ሠራተኞች የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያውን ሩብ...