ለሕፃናት

Date:

ከውልደት እስከ ስድስት ወር ድረስ ሊደረግላቸው የሚገባ እንክብካቤ

  • ከእናት ጡት ወተት ውጪ ሌላ ተጨማሪ ምግብም ይሁን ፈሳሽ አለማስጀመር፤
  • በየሁለት ሰዓቱ የእናት ጡት ወተት  መስጠት፤ 
  • የእናት ጡት ወተት በተገቢው መጠን እያገኙ መሆኑን ማረጋገጥ፤
  • እናትየዋ በሃኪም የተለየ የጤና እክል ከሌለባት በስተቀር መደበኛ የሆነውን የጡት ማጥባት ስርዓት መቀጠል፤
  • ልጆች ስድስት ወር እስኪሞላቸው ድረስ ሌላ ምግብ ማስጀምር  ብዙ ወይም በቂ የእናት ጡት እንዳያገኙ ሊያደርጋቸው ይችላል፤
  • ለልጆች የላም ወተት ከአንድ ዓመት በታች ማስጀመር የሚያስከትላቸው የጤና ጉዳቶች
  • ዝቅተኛ የአይረን መጠን ስላለው ለደም ማነስ ችግር ያጋልጣል፤
  • ከፍተኛ የፕሮቲን ይዘት ስላለው ለስኳር ህመም ያጋልጣቸዋል፤
  • የህጻናት ሆድ ድርቀት ሊያስከትል ይችላል፤
  • የወተት አለርጂ እንዲከሰት ያደርጋል፤
  • ላክቶዝ ንጥረ-ነገር በሰውነት ውስጥ አለመኖር በወተት ውስጥ ለሚገኘው የላክቶዝ ንጥረነገር መብላላት አለመቻል ያጋልጣቸዋል፤ እንዲሁም ተቅማጥን ለመሳሰሉ የጤና እክሎችን ሊያስከትልባቸው ይችላል፡፡

ከስድስት እስከ አስራ ሁለት ወራት ዕድሜ ያሉ ህጻናት መጠቀም ያለባቸው፤

እድሜያቸዉ ከ 6-8 ወር ለሆኑ ህፃናት ተጨማሪ ምግቦችን በፈሳሽ መልክ (እንደ አጥሚት) በቀን ከ2-3 ጊዜ እንዲሁም ከ8-12 ወር ለሆናቸዉ በከፊል ጠጣር መልክ (እንደ ገንፎ) በቀን 4-5 ጊዜ መመግብ ያስፈልጋል፡፡ በዚህ የዕድሜ ክልል ዉስጥ ጡት ማጥባት የሚቀጥል ሲሆን፣ ነገር ግን የእናት ጡት ወተት መጠን እየቀነሰ የሚሄድበት ጊዜ ስለሆነ ለህፃናት የሚሰጠዉ ተጨማሪ ምግብ በዓይነትም በመጠንም በደንብ መጨመር አለበት፡፡ ተጨማሪ ምግቦችን በጠጣር መልክ (እንደ እንጀራ፣ ዳቦ፤ እንቁላል፣ ሥጋ፣ ወዘተ የቤተሰብ ምግቦችን) መጀመርም  ይቻላል፡፡

በሕፃናት ላይ የሚከሰት የአፍ ውስጥ ፈንገስ

የህፃናት የአፍ ውስጥ ፈንገስ የሚከሰተው ፈንገሱ በአፍ ውስጥ አድጎ በሚፈጥረው ኢንፌክሽን ምክንያት ነው፡፡ ይህ ኢንፌክሽን ብዙን ጊዜ ህፃናት ለከፋ ጉዳት የማይጥል ቢሆንም አልፎ አልፎ ግን ከባድ የጤና ችግር የሚሆንበት አጋጣሚ ይፈጠራል፡፡ በተለይ የተፈጥሮ የበሽታ የመከላከል አቅማቸው በተለያዩ ምክንያቶች የተዳከመ ከሆነ ኢንፌክሽኑ ወደ ተለያየ የሰውነት ክፍላቸው በመዛመት ውስብስብ የጤና ችግር የማምጣት እምቅ  አለው፡፡ በተመሳሳም ከሰው ወደ ሰው በቀላሉ ይተላለፋል፡፡

የአፍ ውስጥ ፈንገስ መንስኤዎች በልጆች ላይ

ካንዲያሲስ ፈንገስ አልቢካንስ ሲ በተባለ ፉንገስ አማከኝነት ሊከሰት ይችላሉ፤ እናቶች ብዙን ጊዜ ወተት እንዳይፈስ በማለት ጡታቸውን የሚሸፍኑባቸው ነገሮች አማካኝነት ባክቴሪያዎች ሊፈጠሩ ይችላሉ፡፡ በእርግዝና ጊዜ እናት ማህፀን ኢንፌክሽን ተጋልጣ ሳትታከም ከቀረች በምቶልድበት ሰአት ከስዎ ወደ ልጁ በመተላለፍ ልጁ ላይ የአፍ ውስጥ ፈንገስ ሊያስከትልበት ይችላል እናት በምታጠባበት ወቅት ህመም እና ከጡቷ ጫፍ የሚወጣ ፈሳሽ ካለ ከወተት ወጪ እነዚህ ካሉ ኢንፊክስን ተፈጥሮ ሊሆን ስለሚችል በሚያጠቡበት ወቅት ወደ ህፃኑ ስለሚተላለፍ የአፍ ውስጥ ፈንገስ ሊያስከትልበት ይችላል ስለዚህ ህክምና ማድረግ ይኖረባቸዋል::

የአፍ ውስጥ ፈንገስ ምልክቶች

ነጭ ወይም ቢጫ ቀለም ያላቸው ያበጡ ነገሮች በትንሽ ቦታ ላይ ውስጠኛው ጉንጭ ክፍል፣ በምላስ፣በቶንሲሎች፣ በድድ ወይም በከንፈር ላይ ይወጣሉ፡፡ እብጠቱ በሚፋቅበት ጊዜ አነስተኛ ደም ይወጣዋል፤ በአፍ ውስጥ ቁስል ወይም የማቃጠል ስሜት ይፈጠራል፤

የጥጥ ስሜት አፍ ውስጥ መሰማት

በአፍ ጥግ ላይ መድረቅና የቆዳ መሰንጠቅ ሊያጋጥም ይችላል፤ ለመዋጥ መቸገር የአፍ መጥፎ ጠረን ሊፈጠር ይችላል፡፡ ምግብ የማጣጣም አቅም መቀነስ ወይም ጣእም ማጣት አንዳንዴም የምግብ መውረጃ ትቦ (ኦሶፋገስ) በዚህ ኢንፌክሽን ሊጠቃ ይችላል፡፡

በቤት ውስጥ ማድረግ የምንችለው ምንድን ነው

የህፃናቱን እድሜ ባማከለ መልኩ ለልጆች እርጎን መስጠት እንችላለን፡፡ እረጎ ላክቶስ በሲላይ የተባለ እጥረ ነገርን ስለያዘ ፈንፈፉን ለመቀነስ ይረዳናል፡፡ ለብ ባለ ውሃ ላይ ጨው በመጨመር አካባቢውን መጥረግ፤

ሕክምናው

የአፍ ውስጥ የህፃናት ፈንገስ ለማከም የጤና ባለሙያዎ የሚታዘዙ መድኃኒቶችን ይኖራሉ፡፡ እነዚህ መድኃኒቶች ፀረ- ተዋህሲያን መድኃኒቶች ሲሆኑ ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚጠይቁና በትክክል ሊወሰዱ የሚገባቸው ናቸው፡፡

ዶክተር አለ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የጣሊያን የመከላከያ ስምምነቶችና የፖለቲካዊ ድጋፎች

በመካከለኛው ምስራቅ እየተባባሰ የመጣውን የጸጥታ ስጋት ተከትሎ፣ ጣሊያን ለባህረ...

የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ”ንዋይ” የተሰኘ መተግበሪያን ይፋ አደረገ

የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ ዜጎች...

የነዳጅ እጥረት አሽከርካሪዎችን ለከፋ እንግልት እየዳረገ ነው

በአዲስ አበባ እና በልዩ ልዩ የክልል ከተሞች የሚስተዋለው የነዳጅ...

ሼክ ኢብራሂም ቱፋ በኢራን ኤምባሲ በመገኘት ሀዘናቸውን ገለጹ

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሼክ ኢብራሂም...