የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት እና የኢትዮጵያ ባንኮች ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ አቤ ሳኖ ከቀድሞው የአሜሪካ ባንኮች ማህበር ሊቀመንበር ሚስተር ኬኔት ኬሊ ልምዳቸውን ባጋሩበት መድረክ ተገኝተው ነበር።
ሚስተር ኬሊ በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኢምባሲ ባዘጋጀው በዚህ መድረክ ላይ ባንኮች እንዴት ማደግ፣ መወዳደር እና ደንበኞቻቸውን ማገልገል እንዳለባቸው በአሜሪካ የባንክ ስርዓት ካላቸው ልምድ የቀሰሙትን እውቀት አካፍለዋል።
“የወደፊት የባንክ አገልግሎት ሁኔታ የሚወሰነው በባንኮች ሳይሆን ሊሰጡ በሚችሉት እድል ላይ በመመርኮዝ ነው” ብለዋል ሚስተር ኬሊ።
የአሜሪካ ኢምባሲ ኢትዮጵያ የፋይናንስ ሴክተሩን ለውጭ ባንኮች ክፍት ማድረጓን ያደነቀ ሲሆን፤ ይህም የብድር፣ የቁጠባ እና የኢንቨስትመንት ተደራሽነት እንደሚያሰፋ እና ለኢትዮጵያውያንም ሆነ ለአሜሪካውያን እድል እንደሚፈጥር ተናግሯል።
