በኢትዮጵያ በየዓመቱ ዕድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች ከሚሞቱ ሕፃናት መካከል 18 በመቶው በሳምባ ምች በሽታ ምክንያት እንደሚከሰት በጤና ሚኒስቴር የእናቶች፣ ሕፃናትና አፍላ ወጣቶች ጤና አገልግሎት መሪ ሥራ አስፈጻሚ ሲስተር ዘምዘም መሐመድ ተናግረዋል።
መሪ ሥራ አስፈጻሚዋ፡ ይህን የገለጹት ህዳር 11 ቀን 2019 ዓ.ም የዓለም አቀፍ የሳምባ ምች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ18ኛ፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ7ኛ ጊዜ በተከበረበት መርሃ-ግበር ላይ ነው ።
መሪ ስራ አስፈጻሚዋ መርሃ-ግበር እንደተናገሩት፤ በኢትዮጲያ በየዓመቱ ከ45 ሺህ በላይ ሕፃናት በሳምባ ምችና በተቅማጥ ምክንያት ሕይወታቸው ያልፋል፡፡
ሚኒስቴሩ ችግሩን ለመቅረፍ በጤና ጣቢያዎችና ጤና ኬላዎች የተቀናጀ የሕፃናት ሕክምና አገልግሎት እንዲሰጥ የማድረግ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
ይሁን እንጂ ሕፃናት የሳምባ ምች ምልክት ሲያሳዩ ወደ ጤና ተቋም የመውሰድ ባህል ዝቅተኛ መሆን አሁንም እንቅፋት መሆኑን ጠቁመዋል።
አያይዘውም የክልል ጤና ቢሮዎች በቂ በጀትና ባለሙያ እንዲመድቡ፣ አጋር ድርጅቶችና የሙያ ማኅበራትም የተጀመረውን የመከላከልና የሕክምና ሥራ በጋራ መስራት እንደሚገባ መሪ ሥራ አስፈጻሚዋ ጥሪ አሳስበዋል።
