መጋቢ አዲስ እሸቱ ለአይ ሾው ስፒድ እና ቢዮንሴ በቤተክርስቲያን ለተደረገላቸው አቀባበል ጠንካራ ሂስ ሰነዘሩ

Date:

“እግዚአብሔርም በ30 ብር ተሽጧል”

በሰይፉ ሾው ላይ እንግዳ የነበሩት መጋቢ አዲስ እሸቱ፣ ሰሞኑን አሜሪካዊው ዩቲዩበር አይ ሾው ስፒድ (IShowSpeed) በኢትዮጵያ ያደረገውን ጉብኝት ተከትሎ፣ ታዋቂ ሰዎች ወደ ኃይማኖት ተቋማት ሲመጡ ስለሚደረግላቸው “የተጋነነ አቀባበል” ጠንካራ ትችት ሰነዘሩ።

መጋቢ አዲስ፣ ዝነኞች አገሪቱን መጎብኘታቸው መልካም ቢሆንም፣ የኃይማኖት ተቋማት ግን ማንነትን “ማበጠር እና መለየት” እንዳለባቸው አሳስበዋል።

ሰሞኑን መነጋገሪያ ስለሆነው “አይ ሾው ስፒድ” ሲጠየቁ፣ “ይሄን ልጅ አይናማዎች ናቸው የሚያውቁት፤ ለጆሮ የሚገባ ነገር የለውም፤ ዝም ብሎ ነው የሚጮኸው” በማለት የይዘቱን ጥልቀት የሌለው መሆን በሽሙጥ ገልጸዋል። አያይዘውም ዓለማችን ቁምነገር ከሰራው ይልቅ ለመዝናኛው ቦታ የምትሰጥበት “የኮስሞቲክስ ዓለም” ሆናለች ሲሉ ወቅሰዋል።

“የመጨረሻውን ዘመናዊ ቦይንግ አውሮፕላን ካመረተው ሳይንቲስት ይልቅ፣ እዛ አውሮፕላን ላይ ተሳፍሮ ‘ደህና ዋላችሁ’ ያለ አርቲስት የበለጠ ይከበራል” ያሉት መጋቢ አዲስ፣ ትውልዱም ሆነ አስተሳሰቡ “ፋስት ፉድ” (ፈጣን ምግብ) እንደሆነበት አብራርተዋል።

“አሁን ፋስት ፉድ ፈረንጆቹ ስራ ስለበዛባቸው ‘ቀባ ቀባ’ አድርጎ መብላት ነው፤ የእኛም አስተሳሰብ እንደዛው ሆኗል። ጠንከር ያለ ሃሳብ መስማት አንፈልግም። ለዚህም ነው ጠጠር ያለ ሃሳብ የሚያቀርቡ ደራሲያን ሳይቀር ለመኖር ሲሉ ወደ ኮሜዲ ያኮበኮቡት” ብለዋል።

በተለይም ከዚህ ቀደም ድምፃዊት ቢዮንሴ ወደ ኢትዮጵያ በመጣችበት ወቅት “ጃንጥላ ተይዞላት” የተደረገውን አቀባበል በማስታወስ፣ የሃይማኖት ተቋማት ታሪካዊ ቦታዎችን ለጎብኚ ማሳየታቸው ተገቢ ቢሆንም፣ ክብርን በሚያወርድ መልኩ መቀበል ግን ስህተት መሆኑን ጠቁመዋል።

“ቢዮንሴ በመጣች ጊዜ ሰው ‘በሰባት ስላሴ በአስር ቢዮንሴ’ ብሎ ተረተ። ዝነኞች እንደ ሰው፣ እንደ ቱሪስት ላሊበላንና አክሱምን መጎብኘታቸው ተገቢ ነው። ነገር ግን በዛ ልክ ሃይማኖትን አዋርዶ፣ ዝቅ አድርጎ ‘ሸብ ረብ’ ማለቱ ብዙ አትራፊ አይመስለኝም” ሲሉ ተናግረዋል።

መጋቢ አዲስ እሸቱ መልዕክታቸውን ሲቋጩም፣ እንዲህ አይነት ተግባር የሚፈጽሙ አካላት ጥቅምን አስበው ከሆነ፣ “ዓለም ገንዘብ ከተገኘ እግዚአብሔርም በ30 ብር ተሽጧል” በማለት ጠንካራ መልዕክት አስተላልፈዋል።

(ዘ-ሐበሻ ሕይወት)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ነገ በፓርላማ ተገኝተው ማብራሪያ ይሰጣሉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመጪው ሐሙስ ህዳር 17...

ከፍተኛ የወጪ ንግድ ገቢ ያስመዘገቡ ድርጅቶች ተሸለሙ

በጥራጥሬና ቅባት እህሎች ዘርፍ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ገቢ ያስገኙ...

ዓለም አቀፉ ሽልማት ለጋዜጠኛ ይስሐቅ በላይ ተሰጠዉ

ዓለም አቀፉ ኦሎምፒክ ኮሚቴ (IOC) በ4ኛው የዓለም የወጣቶች ኦሎምፒክ...

የተመድ ዋና ፀሐፊ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ስጋቶችን ለመቆጣጠር ዓለም አቀፍ ትብብር ጠየቁ

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬስ፣ የሰው ሰራሽ...