ማርታ ዓለማየሁ በዓለም አትሌቲክስ የዓመቱ ምርጥ ታዳጊ ኮከብ አትሌት ሽልማት በሴቶች የመጨረሻ 3 ዕጩዎች ውስጥ ተካተተች
ኢትዮጵያዊቷ ታዳጊ አትሌት ማርታ ዓለማየሁ፣ የዓለም አትሌቲክስ ባዘጋጀው የ2026 የዓመቱ ምርጥ ታዳጊ ሴት ኮከብ ወይም ‘ራይዚንግ ስታር’ ምርጫ የመጨረሻ 3 ዕጩዎች ዝርዝር ውስጥ ተካተተች::
የዓለም አትሌቲክስ ዛሬ ይፋ ባደረገው ዝርዝር ዕጩዎቹ ዘንድሮ ከ20 ዓመት በታች ውድድሮች ላይ ላሳዩት ድንቅ ብቃት እውቅና ለመስጠት መመረጣቸውን አስታውቋል
