በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አዳዲስ የዋና ክፍልና የክፍላተ ከተማ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጆች ምድባ ተደረገ።
የተመደቡት የሥራ ሐላፊዎች ቤተ ክርስቲያን የሰጠቻቸውን አደራና ተልእኮ በአግባቡ እንዲወጡ ይጠበቃል።
የተመደቡት የሥራ ሐላፊዎች በሀገረ ስብከቱ ዋና ጸሐፊን ጨምሮ የ7 ዋና ዋና ክፍል ሐላፊዎች፣ ሁለት ክፍላተ ከተማ ቤተ ክህነት እንዲሁም ምክትል የካህናት አስተዳደር ዋና ክፍል ምክልት ሐላፊን የሚያካት ነው።
በዚህ መሠረት፦
1.መልአከ ምሕረት ዘካርያስ ሐዲስ –💠የሀገረ ስብከቱ የካህናት አስተዳደር ዋና ክፍል ሐላፊ
(ቀደም ሲል የካ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የነበሩ)
2.መልአከ ገነት ልሣነ ወርቅ ተስፋ –💠የሀገረ ስብከቱ የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ ዋና ክፍል ሐላፊ
(ቀደም ሲል የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የነበሩ)
3.መምህር ጥዑመ ልሳን እንየው –💠የሀገረ ስብከቱ የማኅበራት ማደራጃ ዋና ክፍል ሐላፊ
(ቀደም ሲል የሀገረ ስብከቱ የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ ዋና ክፍል ሐላፊ ነበሩ)
4.ሊቀ ልሣናት በዳሳ ቶሎሳ –💠የሀገረ ስብከቱ የሰው ሀብት አስተዳዳር ዋና ክፍል ሐላፊ
(ቀደም ሲል በጠቅላይ ቤተ ክህነት የሊቃውንት ጉባኤ አባል)
5.ኢንጅነር መ/ር ቴዎድሮስ እያዩ —
💠የሀገረ ስብከቱ የዕቅድና ልማት ዋና ክፍል ሐላፊ
(ከቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ )
6.ወ/ሮ ወጋየሁ ሙሉጌታ –💠የሀገረ ስብከቱ ሒሳብና በጀት ዋና ክፍል ሐላፊ
(ከቤቶች አስተዳዳርና ልማት ድርጅት )
8.መጋቤ ሰናያት ዮናስ ስንታየሁ –💠የሀገረ ስብከቱ ጠቅላላ አገልግሎት ዋና ክፍል ሐላፊ
(ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት )
8.መጋቤ ብሉይ ድረስ ጌታሁን
💠የሀገረ ስብከቱ ዋና ጸሐፊ
9.መልአከ ምሕረት በቃሉ ወርቅነህ —💠የየካ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ
(ቀደም ሲል የጠቅላይ ቤተ ክህነት የትምህርትና ማሰልጠኛ መምሪያ ምክትል ሐላፊ)
10.መጋቤ ሥርዐት ሣህሉ የማታ –💠 የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ
(ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት )
11.መምህር ሰሎሞን ንጉሤ –የሀገረ ስብከቱ የካህናት አስተዳዳር ዋና ክፍል ምክትል ሐላፊ
(ከለሚኩራ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት የስብከተ ወንጌል ክፍል ሐላፊ የነበሩ)
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ አገልግሎት አዲስ ለተመደቡት የሥራ ሐላፊዎች የመልካም የአገልግሎት ጊዜ እንዲሆንላቸው ይመኛል።
ነሐሴ ፲፰/፳፻፲፰ ዓ/ም አ/አ/ሀገረ ስብከት ሚዲያ
